በክልሉ በውሃ፣ መስኖና ቆላማ አከባቢዎች ፍትሀዊ የልማት ተደራሽነት ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ይሻል፦ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሀ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢዎችና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል። በመድረኩ፤ በውሃና መስኖ፣ቆላማ አከባቢ እእንዲሁም የአከባቢ ጥበቃ ዘርፍ በክልሉ የተሰሩ እና እየተሰሩ ባሉት ዝርዝር ተግባራት ላይ ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በዚህም፥ ባለፉት አራት ዓመታት የክልሉ ምሥረታ አነስተኛ የነበረውን የውሃ…
