Trendings

የ’World Without Hunger’ ጉባኤ ተሳታፊዎችን እንኳን ወደ አፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና በሰለም መጣችሁ እላለሁ።

አለምአቀፍ መሪዎችን፣ ባለሞያዎችን እና የጉዳዩ ተቆርቋሪዎችን በአንድ ላይ በማምጣት እንዲወያዩ በማድረግ የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ። በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ዓመታት በግብርና ሽግግር እና ምርታማነት ላይ በማተኮር የሠራነው ሥራ የታረሰ መሬታችን እጥፍ በማድረስ ከፍ ያለ እሴት ባላቸው የኢንደስትሪ አዝርዕት ምርት ላይ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች አስገኝቷል። በሚቀጥሉት ቀናት…

Read More

የክልሉ ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በተጨባጭ እንዲረጋገጥ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመቀራረብ እየተሰራ ነው፦አቶ ነጋ አበራ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የ3ኛ ዙር የጋራ ምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው። በምክክር መድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራ የክልሉ መንግስት ፈጣንና ቀልጣፋ የልማት ስራዎችን ለህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ በርካታ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት እየሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል። በዚህም የክልሉ ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት…

Read More

ሀገራዊ ምክክሩ በሀገራችን እስከአሁን የነበሩ ችግሮች በንግግርና በምክክር ለመፍታትእጅግ ጠቃሚ ነው፦ አስተያየት ሰጪ መምህራንና የመንግሥት ሠራተኞች

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትናንት ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም በጀመረው አጀንዳ ማሰባሰቢያና ተወካይ መረጣ መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ በክልሉ ከሁሉም ዞኖች የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ከትላንት ከሰዓት ጀምረው አጀንዳዎቻቸውን በቡድን ሲያደራጁ ቆይተዋል፡፡ በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙ መምህራንና መንግሥት ሠራተኞች የምክክር ሂደቱ የሀሳብ የበላይነትንና ነፃነትን ለማረጋገጥ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ ከተሳተፉት መምህራን መካከልም መ/ር ንጉሴ ዓለሙ ከካፋ ዞን…

Read More

የወረዳ የማህበረሰብ ወኪሎች በአጀንዳዎቻቸው ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

#ደቡብ_ምዕራብ_ኢትዮጵያ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ የማህበረሰብ ወኪሎች ከትላንት ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም ከሰዓት ጀምረው ከወከሉት ማህበረሰብ ይዘዋቸው የመጡ አጀንዳዎችን በውይይት በማደራጀት ላይ ናቸው፡፡ በዚህ የምክክር መድረክ ከ57 የክልሉ ወረዳዎች የተወጣጡ 1003 የሚሆኑ የዘጠኝ የማህበረሰብ ክፍል ወኪሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡ እነዚህ የወረዳ የማህረሰብ ክፍል ወኪሎች ምክክራቸውን እስከ ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም ድረስ…

Read More

ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ ለደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የቦርድ አመራር ምደባ ሰጡ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት በወጣ አዋጅ የተቋቋመዉ የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ምደባ ሰጥተዋል። በዚህ መሠረት 1.አቶ ጸጋዬ ማሞ …..ሰብሳቢ 2.አቶ ነጋ አበራ…….ም/ሰብሳቢ 3.አቶ ፋጂዮ ሳፒ…… አባል 4.አቶ የሺዋስ ዓለሙ….አባል 5.አቶ አንድነት አሸናፊ….አባል 6.አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ…….አባል የሚዲያ ኔትወርክ የቦርድ አመራር ሆነዉ ተመድበዋል።

Read More

ኢትዮጵያ ያዘጋጀችው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ኮንፈረንስ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፈተ

ኢትዮጵያ ያዘጋጀችው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ኮንፈረንስ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፍቷል። ይህንን ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ኮንፈረንስ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም እና የመሀመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ዶክተር ከሊፋ ሙባረክ ከፍተውታል። በኮንፈረንሱ ላይ ከ16 ሀገራት የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶችና የተቋማት መሪዎች እየተሳተፉ ነው። ኮንፈረንሱ በልዩ ልዩ መርሀ ግብሮች እስከ ነገ…

Read More

ዲጂታል ኢትዮጵያ ዕውን እንዲሆን የሳይበር ደህንነትን የማረጋገጥ ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው -የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

ዲጂታል ኢትዮጵያ ዕውን እንዲሆን የሳይበር ደህንነትን የማረጋገጥ ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ትዕግስት ሀሚድ አስታወቁ። ለ5ተኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው አገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ዛሬ በድሬደዋ በፓናል ውይይት እየተከበረ ነው። በዚሁ ጊዜ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ትዕግስት ሀሚድ እንዳሉት በዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ ውስጥ የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ…

Read More

በኮንፈረንስ ቱሪዝም በዓለም ላይ ስሟን የተከለችው አዲስ አበባ እንግዶቿን ተቀብላ ለማስተናገድ ተዘጋጅታለች – ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ

በኮንፈረንስ ቱሪዝም በዓለም ላይ ስሟን የተከለችው አዲስ አበባ እንግዶቿን በድምቀት ተቀብላ ለማስተናገድ ተዘጋጅታለች ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ገለፁ፡፡ ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ አዲስ አበባ በዚህ ወር ከምታስተናግዳቸው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች መካከል አንዱ የሆነው “ከርሃብ ነፃ አለም” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባኤ ነገ እንደሚጀምር ገልፀዋል። በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ከጥቅምት 26 እስከ…

Read More

መዓዛማ ቅመማ ቅመሞች በክልላችን

********** በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቅመማ ቅመም ሰብሎች ሽፋን በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ከ86 ሺህ ሄክታር መሆኑ ነው የክልሉ የግብርና ቢሮ መረጃ የሚያመለክተው። እንደ መረጃው በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት ብቻ 418.6 ቶን የቅመማ ቅመም ምርት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል። በክልሉ መዓዛማና መድኃኒት ያላቸው ቅመማ ቅመም በስፋት ከሚመረትባቸው አከባቢዎች አንዱ ደግሞ የሸካ ዞን ነው። በዕድገቱ…

Read More

ምክክሩ ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የ ተሳታፊ ሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ተናገሩ፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ 41 ወረዳዎች እና 16 ከተማ አስተዳደሮች በሀገራዊ ምክክር ኮሚሸን እየተካሄደ ባለዉ የአጀንዳ አሰባሰብ መድረክ ከየማህበራዊ መሠረቶች እየተሳተፉ ያሉት ሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክሩ፣ ሀገር ካገበችበት ውስብስብ ችግሮች ለማላቀቅ ጉሊህ ሚና እንዳለው ተናግረዋል ። በዉይቱ በመሳተፋቸው ደስተኛ ስለመሆናቸውና ምክክሩ ለሴቶች እጅግ በጣም ጠቃሚ መሆኑን የገለጹት የሴቶች ተወካይ…

Read More