አደረጃጀቶች የሕዝብን የሰላምና የልማት ጥያቄ ለመመለስ ፋናወጊ ሆነው ሊንቀሳቀሱ ይገባል፦የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ፍቃዱ ተሰማ

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት “የጠንካራ አደረጃጀት ትጋት ለአገራዊ ህልሞቻችን ስኬት” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረውን የ2017 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቋል፡፡ በመድረኩ ማጠቃለያና የስራ መመሪያ የሰጡት በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ፍቃዱ ተሰማ አደረጃጀቶች ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ እንዲሁም ልማትን በማረጋገጥ ሚናቸውን በመለየት እስከታችኛው የህብረተሰብ…

Read More

የምክክር ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር አስተዋጽኦ አለው – የአውሮፓ ህብረት

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲፈጠር በማድረግ ገንቢ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የአውሮፓ ህብረት ገለጸ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኢመስበርገርን ተቀብለው አነጋግረዋል። ሚኒስትሩ የአውሮፓ ሕብረት ኢትዮጵያ በማኀበረ-ኢኮኖሚ መስኮች ለማሻሻል ለምታደርገው ጥረት ቁልፍ አጋር መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከሕብረቱ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደምትሰራና በተለይም በልማት ትብብር፣ በንግድ…

Read More

በክልሉ ያሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆችን ተልዕኮን ለማስፈጸም በሚችል መልኩ ማጠናከር ይገባል፦ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ክልላዊ የክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ የንቅናቄ መድረክ ተጠናቋል። በክህሎት መር የንቅናቄ መድረክ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በነበረው ውይይት ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። ተሳታፊዎች ባነሱት አስተያየት በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ብቁና ጥራት ያለው ሰልጣኝን ከማፍራት አንጻር ክፍተቶች መኖራቸውንና ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ጉዳይ ቢሮ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ምዕራፍ ሁለት ማስጀመሪያ አውደ ጥናት በቦንጋ ከተማ አካሂዷል።

አውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የ(LLRP )ፕሮጀክት በምዕራፍ አንድ ፕሮግራም በክልሉ የአርብቶ አደር አካባቢዎች ላይ ከትምህርት ቁሳቁስ አንስቶ እሰከ መሰረተ ልማት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን ገልፀው ለ5 ወረዳዎች ለተከታታይ አምስት ዓመታት የሚውል 17 ሚለዮን 136 ሺ 666.70 ዶላር ለፕሮጀክቱ ማሳኪያ መመደቡን ተናግረዋል። ይህ ትልቅ በጀት የተመደበለት ፕሮጀክት በውጤት…

Read More

በመማር ማስተማር ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ የትምህርት ስራን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው፦ ዶ/ር ደስታ ገነሜ

በመማር ማስተማር ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ የትምህርት ስራን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቤሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ደስታ ገለጹ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከዩኒሴፍ በመተባበር ተደጋግሞ መጠቀም የሚያስችል የንጽህና መጠበቂያ ቁስ ማምረትና መጠቀም ዙሪያ ለተማሪዎች የክህሎት ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል። በስልጠና መርሃ ግብር የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ ዶ/ር…

Read More

በቦንጋ ከተማ የወባ ወረርሽኝ የሚራባባቸውን አካባቢዎች የማጽዳትና ፍሳሾችን የማስወገድ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የወባ ወረርሽኝ ስርጭት ለመግታት “ረቡዕን ለወባ” የሚል የጽዳት ዘመቻ ዛሬ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። እንደ ሀገር የወባ ወረርሽኝ በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ከግንዛቤ በማስገባት በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች የግልና የአካባቢ ጽዳት ዘመቻ ሲደረግ መቆየቱ ይታወቃል። ይህንን አምራቹን ኃይል እየጎዳ ያለውን የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል እንደ ካፋ ዞንም ይሁን እንደቦንጋ ከተማ የተለያዩ የጽዳትና የማፋሰስ ሥራዎች ዛሬም እየተሰሩ ይገኛሉ።…

Read More

ተቋማዊ የመፈጸም አቅምን በማሳደግ ውጤታማ ፖሊሳዊ ተግባራት መከናወቸዉ ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የ2016 በጀት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት አመት ጠቋሚ ዕቅድ ዙሪያ ከዞን፣ወረዳ የፖሊስ አመራሮችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ እየመከረ ይገኛል። በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፖሊሲ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰብስበ ሸዋኖ በ2016 በጀት ዓመት ተቋማዊ የመፈጸም አቅምን በማሳደግና አሰራሮችን በማጎልበት በክልሉ ሁሉም መዋቅሮች ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን መቻሉን…

Read More

ወጣቶች በተሰማሩባቸው የስራ መስኮች ውጤታማ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፦ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

በክልሉ የሚገኙ ወጣቶች በተሰማሩባቸው የስራ መስኮች ጥራት ያለውና በገበያ ተወዳዳሪ ሆነው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናግረዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ክልላዊ የክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ የንቅናቄ መድረክ እንደቀጠለ ነው። በንቅናቄው መድረክ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በክልሉ በርካታ የቴክኒክና…

Read More

የበለፀገች ሀገር የመገንባት ህልማችንን ለማሳካት ተቋማት ከእቅድ በላይ መፈፀም አለባቸው፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

የበለፀገች ሀገር የመገንባት ህልማችንን ለማሳካት ተቋማት ከእቅድ በላይ መፈፀም አለባቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆኑ አስፈጻሚ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት ተገምግሟል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለተቋማት ግንባታ በተሰጠው ትኩረት በርካታ ሀገራዊ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ለአብነትም ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ…

Read More

ሴቶች ሀገረ መንግስት በመገንባት ሂደት ውስጥ ያላቸውን ሚና አጠናክረው ሊወጡ ይገባል፦ አቶ ነጋ አበራ

ሴቶች ሀገረ መንግስት በመገንባት ሂደት ውስጥ ያላቸውን ሚና አጠናክረው ሊወጡ ይገባል ሲሉ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቦንጋ ማዕከል ክልል ተቋማት የሴቶች ሊግ መሰረታዊ ድርጅት የአንደኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ መድረክ እየተካሄደ ነው። የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል መሪ ሀሳብ የመሰረታዊ ድርጅት…

Read More