የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የስራ ዕድል ፈጠራ ተግባራትን ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት ስራዎች ጋር ማስተሳሰር ይገባል፦ አቶ ተስፋዬ እንዳሻው ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ክልላዊ የክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ማድረግ ጀምሯል። በንቅናቄው መድረክ የተገኙት የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እንዳሻው ገበያ መር የክህሎት ልማትን እውን በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን በማረጋገጥ ዜጎች ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቢሮው ተልዕኮውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል። ሀገራዊ ለውጡን ውጤታማ፣ዘላቂና ተቋማዊ በማድረግ ክልላዊ…
