በክልሉ ከ32 ሺህ በላይ ሳይፈቀድ የተያዙ የከተማ መሬት ይዞታዎችን ምዝገባ ማከናወን ተችሏል።-የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሳይፈቀድ የተያዙ እና በማስፋፋት የተያዙ ይዞታዎችን ለማስተካከል በመስተዳደር ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 012/2015 እና መመሪያ ቁጥር 001/2015 በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በተደነገገው መሠረት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ገልጸዋል። የቢሮ ምክትል ኃላፊና የከተሞች መሬት ልማት ማኔጅመንት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጫናቸው ወንድሙ እንደገለጹት በክልሉ ሳይፈቀድ የታያዙ የከተማ መሬት…
