የህዝብ ተጠቃሚነት በሁሉም ዘርፍ እንዲረጋገጥ ተቋማት የህዝብ ውክልና ስራዎችን በተገቢው ሊወጡ ይገባል ፦ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ጸሀይ ዳርጫ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የአስፈጻሚ ተቋማት ዕቅድ አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ እየገመገመ ነው። የህግ፤ ፍትህና መልካም አስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ፤ማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ ፤ግብርና እና ገጠር ልማት፤ከተማና መሠረተ ልማት ዘርፍ ፤እንዲሁም በጀት፤ ፋይናንስና ኦዲት ጉዳዮች ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች ናቸው አፈጻጸሙን እየገመገሙ የሚገኙት። የክልሉ ምክር ቤት…
