ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን “ህፃናት የሚሉት አላቸው እናዳምጣቸው! ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገለጸ
የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገልጿል ፡፡ የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ እንደገለጹት ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ አካል የሆነው የአለም ህጻናት መብቶች ኮንቬንሽን እ.ኤ.አ ኑቬምበር 20/1989 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ፀድቆ በስራ ላይ እንዲውል…
