የበለፀገች ሀገር የመገንባት ህልማችንን ለማሳካት ተቋማት ከእቅድ በላይ መፈፀም አለባቸው፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
የበለፀገች ሀገር የመገንባት ህልማችንን ለማሳካት ተቋማት ከእቅድ በላይ መፈፀም አለባቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆኑ አስፈጻሚ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት ተገምግሟል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለተቋማት ግንባታ በተሰጠው ትኩረት በርካታ ሀገራዊ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ለአብነትም ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ…
