የገንዘብ ሚኒስቴር እና የእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ደረሱ
የገንዘብ ሚኒስቴር እና የእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡ የገንዘብ ማኒስትሩ አህመድ ሺዴ ከባንኩ ፕሬዚዳንት ጂን ሊኩውን ጋር ባደረጉት ውይይት፤ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው የትብብር መስኮች ላይ መክረዋል። እንደ ሀገር እየተሰራበት ባለው የረጅም ጊዜ የእድገት ፕሮግራም፣ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርምና ሌሎችንም ተግባራት ኢትዮጵያ እያከናወነች መሆኑን ለባንኩ አመራሮች አስረድተናል ሲሉ አቶ አህመድ ተናግረዋል።…
