የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በክልሉ የተጀመረውን ሁሉ አቀፍ ተግባርን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ ገለፀ
በሀገራችን የትምህርት ጥራት ላይ እያጋጠሙ ያሉ ስብራቶችን ለመጠገን በመንግስት በኩል በርካታ የሪፎርም ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልም ይህንን የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመፍታት በክልሉ በትምህርት ቢሮ በኩል የጀመሩት በርካታ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የገለፁት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተመር ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ደስታ ገነሜ ለዚህም በክልሉ አጠቃላይ በትምህርት ስርዓቱ…
