የአገልግሎት አሰጣጥን ሰው ተኮር የማድረግና መልካም አስተዳደርን ማረጋገጥ የፓርቲው ዋና ተግባር ይሆናል። አቶ ጸጋዬ ማሞ።
በመንግስት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥን ሰው ተኮር የማድረግና መልካም አስተዳደርን የማረጋገጥ ጉዳይ የፓርቲው ዋና ተግባር ሆኖ የሚቀጥል መሆኑን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጸጋዬ ማሞ ተናገሩ ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2016 የተግባር አፈጻጸምና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጀሙ ከተማ እየመከረ ነው። በፓርቲው የአፈጻጸም…
