የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ በማጠናከር የወጣቶችን ስብዕና ግንባታ ማሳደግና ስራ ዕድል ፈጠራ ማሻሻል እንደሚቻል ተገለጸ::
በኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራው ልዑክ በዞኑ የጪዳ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እንቅሰቃሴዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሰለሞን ሶካ የሚኒስተሩ ዋና ተግባር የወጣቶችን ስብዕና ግንባታ በማሳደግ የተለያዩ አጫጭር ሙያዊ ስልጠናዎችን ወስደው ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው የጪዳ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የጀመራቸውን ተግባራትን ማጠናከርና እንደመንግስትና ህዝብ ለዘርፉ መሻሻል ሁለ ዐቀፍ…
