July 2025
የመሃሉ ዘመን ወጥመድን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰጡት ማብራሪያ
የመሃል ዘመን ማለት በሽግግሩ ማጠናቀቂያና በጸናው ስርዓት መጀመሪያ ላይ ማለት ነው። ስድስት ዓመታት የፖለቲካ ሪፎርም አደረግን የሰፈር ፓርቲ አጥፍተን ብልጽግናን ፈጠርን፣ በየሰፈሩ የነበረን ፓርቲ አምጥተን ብልጽግናን መፍጠር በራሱ ትልቅ እምርታ ነው። እኛ ያደረግነውን እኮ ብዙዎቹ አልቻሉም ገና በማህበራዊ ድረ ገጽ ውስጥ ነው ያሉት። ከተቋማት ሪፎርም ጀምሮ የተሟላ ኢኮኖሚ ሪፎርም ስላደረግን ነው መሃል ያልነው። ይሄ ማለት…
የዋጋ ግሽፈቱ ወደ 14.4.% ዝቅ ብሏል:: ምግብና ምግብ ነክ በሆኑ ምርቶች ላይ ግሽፈቱ ወደ 12% ወርዷል፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
በበጀት ዓመቱ የዋጋ ግሽፈት በ2016 በጀት ዓመት ከነበረው 22% ወደ 14.4% መውረዱንና ከዚህ ውስጥ ምግብና ምክብ ነክ የሆኑ ሸቀጦች ግሽፈት ወደ 12% መውረዱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት ከብሔራዊ ባንክ ዓመቱን ሙሉ ብድር ሳይወሰድ ዓመቱን ማጠናቀቁ፣ በፊስካልና የገንዘብ ፖሊሲ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማሻሻያ ላይ የተወሰደው እርምጃ የዋጋ ግሽፈትን ለመቆጣጠር ከፍተኛ…
በእኛ በኩል አንድ ጥይት አይተኮስም:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በኤርትራ በኩል ከሰሞኑ ጦርነት ይጀመራል የሚል ነገር ቢኖርም ከእኛ በኩል ግን አንድ ጥይት እንደማይተኮስ ለምክር ቤቱ ለመግለጽ እውዳለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ በንግግር እንጂ በግጭት አታምንም፤ ሌላውም ወገን በዚህ ቢመራ የተሻለ ይሆናል ከዚህ ውጪ ያለው ነገር አይጠቅመንምም” ነው ያሉት። ፍላጎታችን ያለንን ተካፍለን ከወንድም ሕዝቦች ጋር በጋራ እየለማን መኖር ነው፤ ይሄን…
“ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት።
“ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢኮኖሚ፣ የሕዝብ ብዛት እና የዘመነ ሰራዊት ያላት ሀገር ናት። የማንሰራራት ጉዟችን እንዳይስተጓጎል ከሁሉም ጎረቤቶቻችን ጋር በሰላም መኖር እንፈልጋለን። ባለፉት ሰባት ዓመታት አንድም ግጭት ከጎረቤት ሀገራት ጋር አላደረግንም። በትብብር አብሮ ማደግ ነው ፍላጎታችን። ሰላማችንን የሚያሰጋ ነገር ካለ ግን ኢትዮጵያ ራሷን ለመከላከል በቂ አቅም አላት። ኢትዮጵያን ለማበልፀግና ለማጽናት የሚያበቃ በቂ አቅም…
የ2018 የፌዴራል መንግሥት በጀት 1 ነጥብ 93 ትሪሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡ ምክር ቤቱ በስብሰባው የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ በዚህም የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀት 1 ነጥብ 93 ትሪሊየን ብር ሆኖ ጸድቋል፡፡ የ2018 በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት ረቂቅ በጀት ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የፊሲካል ፖሊሲን…
የተሳሳተ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው እና አውርቶ አደሮች ዋነኛ የኢትዮጵያ ችግሮች ናቸው፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ችግር ዋነኛው መንስኤ፤ የተሳሳተ የፖለቲካ አመለካከት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። የዚህ ዋና ዋና ማሳያዎች ከሆኑት መካከል አንዱ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የስንፍና ፖለቲካ የወለደው ችግር እንደሆነ ጠቅሰዋል። የስንፍና ፖለቲካ ግጭት፣ ፀብ፣ ተቃርኖን ይወልዳል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ የአሁኖቹን ፖለቲከኞች ከድሮ ዘመን መሳፍንቶች እና መኳንንቶች ጋር አመሳስለዋቸዋል። “የድሮ መኳንንቶች…
“ኤርትራ ሉዓላዊ አገር ናት፤ በግድ የኢትዮጵያ አካል እንድትሆን አንፈልግም” ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፤ ኤርትራ ሉዓላዊ አገር ናት፤ በግድ የኢትዮጵያ አካል እንድትሆን እኛ አንፈልግም ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ አገር መሆኗን በመግለጽ፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ግን በጎረቤቶቿ መከበር አለበት ሲሉ ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ እና የጎረቤቶቿ እሳቤ አንዳችን ለሌላችን በጣም አስፈላጊ መሆናችንን መገንዘብ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሰላም ካጣች ከተጎዳች…
“ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዳይገቡ እያደረጉ ያሉ ኃይሎችን መልክ ማስያዝ ያስፈልጋል።”፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸውም፤ ሰላም ሁሌም የሚገነባና ተከታታይ ስራ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የሚገባትን ሰላም እንዳልያዘች ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዜጎች በሰላም ወጥተው ሰርተው እንዳይገቡ እያደረጉ ያሉ ሀይሎችን በተባበረ ክንድ መልክ ማስያዝ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡ ጥይት ባይተኮስም የሰውን…
