የመምህራን አቅም ግንባታ ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ መሆኑ ተገለጸ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የትምህርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ በተገኘው የበጀት ድጋፍ በተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ፕሮግራም (CPD) ላይ ለባለሙያዎችና ለመምህራን በቦንጋ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ። በስልጠናው መግቢያ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊና የመ/ራን ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማርቆስ ቡልቻ የስልጠናው ዓላማ በመ/ራን ልማት ላይ የሚታየውን ማነቆዎች በመለየት መ/ራንን በይዘት፣ በስነ ዘዴና በሌሎች…
