የክልሉ ኦዲት ግብረ ኃይል በቤንች ሸኮ ዞን የክዋኔና የአካባቢ ኦዲት አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ገመገመ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ አስራት አበበ የክልሉ ምክር ቤት የተለያዩ የኦዲት ውጤቶችን በጋራ ከገመገመ በኃላ በክዋኔ ኦዲት የተሰሩ ስራዎች በተጨባጭ ታች ተወርዶ መታየት እንዳለባቸው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል ። መድረኩ በዋናነት የኦዲት ግኝት በአግባቡ ስለመመለሱ ማረጋገጥ እና በዚህ ላይ በአግባብ ያልፈጸሙ አካላትን ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ይሆናል…
