ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ለ1,447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1,447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ። ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የመረዳዳት እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል። ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢድ አልፈጥር በዓል የትዕግስት፣ የመስዋዕትነት፣ የርኅራኄ እና የአንድነት እሴቶች የሚጎሉበት ልዩ ወቅት መሆኑን ጠቁመዋል። በተለይም በታላቁ…

Read More

በሚዛን አማን ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 5,000 ሊትር ናፍጣ በቁጥጥር ስር ዋለ

​ በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 5,000 ሊትር ናፍጣ በቁጥጥር ስር ማድረጉን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ። በከተማዋ ውስጥ የሚታየውን ህገ-ወጥ የነዳጅ ዝውውር ለመግታት የሚደረገው የተቀናጀ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል። ​የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስማረ ቶቲ እንደገለጹት፤ ከፖሊስና ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ህገ-ወጥ የነዳጅ ዝውውርን ለመቆጣጠር የተጀመረው…

Read More

በሸካ ዞን የፓርቲና የልማት ስራዎች አፈጻጸም እየተገመገመ ነዉ

‎በሸካ ዞን በሁሉም መዋቅሮች የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈጻጸም የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች አካላት በተገኙበት በቴፒ ከተማ እየተገመገመ ይገኛል። የፓርቲና የመንግስት ኢንሼቲቮችን በበላይነት በመምራትና ውጤታማነታቸው ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ አመራሩ በባለቤትነት በመምራት የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንዲያስችል የጋራ መግባባት ላይ እንዲደረስ ያለመ የውይይት መድረክ እንደሆነም ተጠቁሟል። በወረዳና በከተማ አስተዳደር የተደረጉ የአመራር ግምገማና ምዘና አፈጻጸም እየተገመገመ ይገኛል።…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወር የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ጤናማ ዜጋን ለመፍጠር ኢንስቲትዩቱ በክልሉ የጤና ስጋት የሆኑ በሽታዎችን የመለየት፣ ቅድመ ዝግጅት የማድረግ፣ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመስጠትና የመከላከል ስራ እየሰራ ያለው አንጋፋ ተቋም መሆኑን አብራርተዋል። የመረጃ ጥራት ለማሻሻልና ከዚህ በመነሳት አስፈላጊውን የግብዓት ችግርን ለማቅረብ፤ መረጃውን ዲጂታላይዝ በማድረግ የመረጃ ጥራትን ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ…

Read More

የ1447ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል ጨረቃ የታየች እንደሆነ ነገ ሐሙስ፤ ካልታየች ደግሞ ዓርብ ይከበራል

የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ባወጣው መግለጫ፣ የ1447ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል የሸዋል ጨረቃ ዛሬ ምሽት ከታየች ነገ ሐሙስ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከበር መሆኑን አስታውቋል። ሆኖም ዛሬ ምሽት ጨረቃ ካልታየች የረመዷን ፆም 30 ቀናት ተሟልቶ በዓሉ የፊታችን ዓርብ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት እንደሚከበር ጠቁሟል። ፍርድ ቤቱ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን…

Read More

የነዳጅ ምርትን በአግባቡ ማስተዳደርና በቁጠባ መጠቀም ያስፈልጋል፦ አቶ ማስረሻ በላቸው

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የነዳጅ ምርት ሥርጭትና አስተዳደር እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት ውይይት በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። ውይይቱ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊና አካባቢያዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ የነዳጅ ምርት ሥርጭትና አስተዳደርን ለማሻሻል እና ወጥነት ያለው የቁጥጥርና አስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ ነው። በውይይቱ የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትልና ንግድና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አምዴ…

Read More

ጠንካራ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት የትምህርት ጥራትን እንደሚያስጠብቅ ተገለጸ

ጠንካራ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ሚናው የጎላ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው በትምህርት አስተዳደር መረጃ ሥርዓት ዲጂታላይዜሽን ላይ ያተኮረ የግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው። የመድረኩ ዓላማ የትምህርት መረጃ አስተዳደር ዘርፉን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ መሆኑ ተመላክቷል። የቢሮው ምክትልና የመማር ማስተማር ዘርፍ ኃላፊ ደስታ ገነሜ (ዶ/ር)፥ በመክፈቻ ንግግራቸው ጥራት ያለው…

Read More

የክልሉ ጤና ቢሮ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነዉ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በንቅናቄ መድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ትውልድ የሚያስቀጥሉና አገር የሚያሻግሩ እናቶችንና ሴቶችን የሚያጠቃውን የማህፀን በር ካንሰር በሽታን በቅድመ ምርመራና በክትባት ለመከላከል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ያስፈጋል ብለዋል። አቶ ኢብራሂም አክለውም በክልሉ በበጀት አመቱ ባለፉት ስምንት ወራት ምርመራ ከተደረጉ 8021 እናቶች 272 እናቶች ላይ የቅድመ ካንሰር ምልክት…

Read More

የሸካ ዞን ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ጉባኤውን በቴፒ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

ጉባኤውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ካሳሁን ምክር ቤቱ በሕገ-መንግሥቱ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰላም ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ዞኑ አሁን ላይ ለሚገኝበት ዘላቂ ሠላም ምክር ቤቱ ጉልህ ሚና መጫወቱን ጠቅሰው ይህንንም አጽንቶ ለማስቀጠል ሁሉም የድርሻውን የመወጣት ኃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል። ​የዘንድሮው ጉባኤ 7ኛው ሀገራዊ…

Read More

የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት ከሌሎች ተቋማት ጋር ጠንካራ ግንኙነት ፈጥሮ እየሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አስታወቀ።

የክልሉ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤ የ3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ እና 3ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ መርምሮ በማፅደቅ እንዲሁም የ2018 ግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በመገምገም ተጠናቀቀ። በግማሽ ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራትን የተመለከተ የፎቶ አዉደ ራዕይ መርሐ ግብርም ተከናውኗል። የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሀገራዊ ሁኔታን ታሳቢ…

Read More