ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ገቢራዊ ያደረገቻቸው ፕሮጀክቶች ለቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደት ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየ ነው፦አፍሪካዊያን ምሁራን
ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ገቢራዊ ያደረገቻቸው ፕሮጀክቶች ለቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደት ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየ ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው አፍሪካዊያን ምሁራን ገለጹ። ፕሮጀክቶቹ አፍሪካን እና ቀጣናውን በኢኮኖሚ ለማስተሳሰር ጉልህ ፋይዳ እንዳላቸውም ምሁራኑ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በዜጎች ርብርብ በራስ አቅም ገንብታ አጠናቃለች። የኒውክሌር ኃይልን ለሠላማዊ ግልጋሎት ለማዋል የሚያስችል ፕሮጀክት፣የነዳጅ ማጣሪያ እና የተፈጥሮ ጋዝን፣ግዙፍ የማዳበሪያ…
