Trendings

በጋራ ለሠሩ መሪዎች ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ምሥጋና አቀረቡ::

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በባሕር ዳር ከተማ ከእርሳቸው ጋር ተገኝተው ሕዝባዊ ውይይቱን ለመሩት የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና ለመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሩ ተሥፋዬ በልጂጌ የክብር ካባ አልብሰዋል። ርእሰ መስተዳድር አረጋ “ወንድሜ ሙስጦፌ በሶማሌ ክልል የሚኖሩ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች እኩል ተከብረው እና ደኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲሠሩ እና እንዲኖሩ ያስቻሉ መሪ ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል። አማራ…

Read More

በቦስተን የኒው ባላንስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይና ለሜቻ ግርማ አሸነፉ::

በቦስተን የኒው ባላንስ የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ እና ለሜቻ ግርማ ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቀዋል፡፡ በ1 ሺህ 500 ሜትር የተወዳደረችው ጉዳፍ ፀጋይ ርቀቱን በ3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ በዚሁ ርቀት የ18 ዓመቷ አትሌት ብርቄ ሀየሎም 3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ43 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ ወጣቷ…

Read More

ኢትዮጵያን ለዜጎቿ ምቹ ማድረግ የሚያስችሉ አስደናቂ የልማት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን አይተናል – ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን::

ኢትዮጵያን ለአሁኑም ይሁን ለቀጣዩ ትውልድ የተመቸች ሀገር ማድረግ የሚያስችሉ የልማትና ግንባታ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን መመልከታቸውን ወደ ሀገር ቤት የገቡ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ተናገሩ። በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከታህሳስ 20 ቀን 2016 እስከ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በሶስት ዙር ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። የመጀመሪያው…

Read More

“የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል በሁሉም የሃገሪቱ የኮሙኒኬሽን መዋቅር ውስጥ ያለው ባለሙያ ፈጣንና ምላሽ ሰጪ ሊሆን ይገባል” የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

“የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል በሁሉም የሃገሪቱ የኮሙኒኬሽን መዋቅር ውስጥ ያለው ባለሙያ ፈጣንና ምላሽ ሰጪ ሊሆን ይገባል” የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመታዊ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የጋራ ጉባኤ ዛሬ ተጀምሯል።በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) መላው የሃገሪቱ የኮሙኒኬሽን መዋቅር ባለፉት ስድስት ወራት የሃገሪቱ ዋና ዋና የልማት…

Read More

ኢትዮጵያ የተዘጋባት በር በመከፈቱ ለዘርፉ ትልቅ ዕድል ነዉ – አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ የተዘጋባት በር በመከፈቱ ለዘርፉ ትልቅ ዕድል መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ የሴክተር አፈጻጸም በወላይታ ሶዶ ከተማ እየገመገመ ነው፡፡ ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) በወቅቱ፥ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ የሁሉም ዘርፎች ደም ስር በመሆኑ በጋራ ልንሠራ ይገባል ነው ያሉት። በዚህም ባለፉት ጊዜያት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሳኩ ተግባራት መፈጸማቸውን…

Read More

“ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን” ዓውደ-ርዕይ ነገ በይፋ ይከፈታል

“ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን” በሚል የሚካሄደው የዲፕሎማሲ ሣምንት ዓውደ-ርዕይ በነገው ዕለት በይፋ እንደሚከፈት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ዓውደ ርዕዩን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እንዲከበር የሁሉም ሕብረተሰብ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። አምባሳደር መለስ (ዶ/ር)÷ “ዲፕሎማሲያችን ከአፍሪካ መዲናነት እስከ ዓለም ዓቀፍ መድረክነት” በሚል ሥያሜ በሚካሄደው ዓውደ-ርዕይ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ…

Read More

የኢትዮ-ሶማሊላንድ የባህር በር ስምምነት በቅንነት የሚወሰድና የሚደገፍ ሀገራዊ አጀንዳ ነው

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው የባህር በር ስምምነት በቅንነት የሚወሰድ ሀገራዊ አጀንዳ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአባላቱ ጋር ምክክር አድርጓል። በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ መካከል በተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት ዙሪያም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከውይይቱ በኋላ ለኢዜአ…

Read More

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያና በሶማሊ ላንድ መካከል የተደረሰዉን ስምምነት አስመልክቶ በምክር ቤቱ ሰብሳቢዉ በኩል መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫዉን የሰጡት የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የተደረሰዉ ስምምነት ሁሉን አቀፍ የትብብርና አጋርነት የሚያጠናክር በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ መስኮች እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ ስምምነት እንደሆነ…

Read More

ኢትዮጵያ የፊታችን ሰኞ ብሪክስን በይፋ በአባልነት ትቀላቀላለች

ኢትዮጵያ የፊታችን ሰኞ ብሪክስን በይፋ በአባልነት ትቀላቀላለች በነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ 15ኛው የብሪክስ አባል አገራት ጉባኤ መካሄዱ ይታወቃል። በነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በተካሄደው 15ኛው የብሪክስ አባል አገራት ጉባኤ ኢትዮጵያ የአምስት አገራት ጥምረት የሆነውን ማህበር ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ የሚታወስ ነው። ጥምረቱ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ግብጽ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ…

Read More

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ለቱሪዝም ዘርፉ መዳረሻዎችን ብቻ ሳይሆን መሰረተ ልማቶችንም አበርክተዋል :-አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ለቱሪዝም ዘርፉ መዳረሻዎችን ብቻ ሳይሆን መሰረተልማቶችን በማበርከት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሚገኙ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ገለጹ። የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነው ጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከትናንት በስቲያ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ጨበራ ዝሆን ዳና ሎጅ በገበታ ለሀገር ከለሙት መዳረሻዎች መካከል መሆኑን…

Read More