Trendings

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አዲስ አበባን “እየፈካች ያለች የአፍሪካ ከተማ” ሲሉ ገልፀዋታል

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት በጆሀንስበርግ ከተማ ባደረጉት ንግግር ላይ በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከተማዋን እጅግ ውብ፣ ፅዱ እና ለኢንቨስትመንት ምቹ እንድትሆን አድርጓታል ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደውን እና የጆሀንስበርግ ከተማ የምታስተናግደውን የጂ 20 የመሪዎች ስብሰባን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ላይ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ ከ10 ቢሊዮን በላይ ችግኞች…

Read More

በስድስት ወራት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

በ2017 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል የኮንትሮባንድና ድንበር ቁጥጥር መምሪያ የሬጅመንት 14 አዛዥ ኮማንደር ጌትነት አበዛ ፤ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመግታት እራሱን የቻለ የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ፖሊስ አደራጅቶ ወደ ሥራ በማስገባት ቀድሞ ከነበረው የተሻለ የአሠራር…

Read More

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች እየተከበረ ይገኛል። ዘንድሮ ቀኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳድሮች በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ እንደሚገኝ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Read More

የኢትዮጵያ ሴቶች ለሀገራቸው የላቀ አበርክቶ አድርገዋል – ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዝዳንት ታዬ ቀኑን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ሴቶች ለሀገራቸው ነፃነት፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ማህበራዊ እሴቶችና ባህሎችን ለማፅናት ያበረከቱት አስተዋጽኦ የላቀ ነው ብለዋል። እንቅፋቶችንና ጎታች እሳቤዎችን በመጣል፣ በመላ አቅማቸው የኢትዮጵያን የመዘመን መንገድ ዋነኛ መሪና ተዋናይ መሆናቸውንም ገልጸዋል። ዘንድሮ ቀኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ…

Read More

በ6 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ በረራ ተደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትናንት ከምሽቱ 5 ሠዓት ጀምሮ በሥድስት ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ በረራ ማድረጉ ተገለጸ፡፡ ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኤርናቪጌሽን አገልግሎት ዘርፍ እነዚህን ሥድስት ዓለም አቀፍ በረራዎች በሴቶች ብቻ እንዲስተናገዱ ማድረጉን በማኅበራዊ ትርሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡ በረራዎቹ በሴቶች ብቻ እንዲሸፈኑ የተደረገው፤ ዓለም አቀፉን የሴቶች አስመልክቶ መሆኑም ተገልጿል ሲል ኤፍ ኤም…

Read More

በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የመንግስት ዋና ዋና አጀንዳዎችን ከማስረጽ አንጻር ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል

በበጀት አመቱ ግማሽ አመት እቅድ በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የመንግስት ዋና ዋና አጀንዳዎችን ከማስረጽ አንጻር ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ “ዓላማ ተኮር፤የተናበበ እና የተቀናጀ የተግባቦት ስርዓት ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና የኦሮምያ ክልል ርዕሰመስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ጋር በአምቦ ወረዳ በነበራቸው ጉብኝት የኬኛ ቤቭሬጅ ፋብሪካን ተመልክተዋል። ፋብሪካው በመጪዎቹ ሶስት ሳምንታት ውስጥ ወደሥራ የሚገባ ሲሆን 3 ሚሊዮን ሄክቶሊትር የማምረት አቅምም አለው።

የአስተዳደር ሥራን ወደ ሕዝብ ለማቅረብ የቀበሌዎች መጠናከር ወሳኝ ነው። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በየአካባቢው ለሕዝብ ቅርብ የሆነ አስተዳደር ለመፍጠር (power devolution) ጥረት እያደረገ ነው። ከዚህ አንጻር በአምቦ ወረዳ የአንድ ቀበሌ እንቅስቃሴ በጉብኝት ወቅት ታይቷል። በዚህ ቀበሌን የማብቃት ተግባር በክልሉ 7342 ቀበሌዎች ተደራጅተዋል። 50,000 የሰው ኃይል ተመድቦላቸዋል። ከዚህ ቀደም በወረዳዎች ተማክለው የነበሩ ሞያዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች በቀበሌ ደረጃ…

Read More

የብልፅግና ፓርቲ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

በአጠቃላይ ሀገራዊ ፓለቲካ ሁኔታ፣ ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ለማሳካትና በፓርቲና በመንግሥት ቅንጅት የሚሰሩ የንቅናቄ አጀንዳዎችን የሚገመግመው መድረክ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ተጀምሯል። በመርሀ ግብሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የዘርፍ አመራሮች የክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የክልል የአደረጃጀት እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ለ3 ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል…

Read More

ራስን በትጥቅ አቅም የመቻል የሪፎርም ስራ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል፦ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

ራስን በትጥቅ አቅም የመቻል የሪፎርም ስራ ተጨባጭ ውጤቶች እየተገኙበት መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ሪፎርም ዋነኛ የትኩረት ማዕከል አንዱ በትጥቅ ራስን መቻል እንደሆነ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ጥይት እና ተተኳሽ ከውጭ ሀገራት ትገዛ እንደነበር ያወሱት…

Read More

የመስኖ ልማት የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመከላከል የጎላ ሚና እንዳለው ተጠቆመ

የመስኖ ልማት የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባሻገር የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመከላከል የጎላ ሚና እንዳለው የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አማካሪ ታየ ሙሉጌታ ኢትዮጵያ ያላትን ውሃዎች በመስኖ ተጠቅማ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል፡፡ በዚሁም ያላትን የውሃ ሀብት እና ሰፊ መሬት ተጠቅማ በመስኖ የምትለማ ሀገር መሆኗን አረጋግጣለችም ነው ያሉት። ከጊዜ ወደ ጊዜ…

Read More