Trendings

“ኢትዮጵያ የአፍሪካ መቀመጫ የሆነችው በአጋጣሚ ሳይሆን ባላት ድንቅ ታሪክ ነው” – የሀገራት አምባሳደሮች

የብሔራዊ ቤተ መንግስት የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጻኢ ጊዜዋ ጋር አስተሳስሮ የያዘ ድንቅ ስራ መሆኑን ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለጹ። የታደሰው ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ከትናንት በስቲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት መመረቁ ይታወቃል። የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችም በብሔራዊ ቤተ መንግስት ጉብኝት አድርገዋል። በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ የኢትዮጵያ እና…

Read More

የዩኒቨርሲቲዎች በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ የሚመደብ ይሆናል -ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለፁ። በትምህርት ዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በተቀናጀ መልኩ ማሻሻል የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል። ስምምነቱን ትምህርት ሚኒስቴርና 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎችና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ፈርመውታል። የትምህርት ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት፥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በመሰረታዊነት ለመቀየር የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ወሳኝ ነው ብለዋል። በተለይም ብቃት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራትና…

Read More

ኢትዮጵያ ለአንካራው ስምምነት ተግባራዊነት ቁርጠኝነቷን ስትገልፅ፤ ሶማሊያም በበኩሏ ስምምነቱ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲተገበር እሻለሁ ብላለች

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዲኤታ አሊ መሐመድ ኡመር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይተዋል። አምባደሳደር ምስጋኑ በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ህዝቦች የማይነጣጠል መፃኢ ዕድል ያላቸው መሆኑን በመግለፅ፤ ሀገራቱ ተባብረው መስራት፣ ችግሮች ሲጋጥሙም ተቀራርቦ መፍትሄ መሻት ይገባቸዋል ብለዋል። ኢትዮጵያ ለአንካራው ስምምነት ተግባራዊ መሆን ቁርጠኛ…

Read More

አገር ተረካቢ ትውልድ በመጤ ባህሎች እንዳይበረዝ በትኩረት መስራት ይገባል-ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ

አገር ተረካቢ ትውልድ በመጤ ባህሎች እንዳይበረዝ በትኩረት መሰራት ይገባል ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ገለጹ። ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል ያለመ አገር አቀፍ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ በድሬዳዋ ተካሂዷል። መርሃግብሩ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና የእግር ጉዞ ተጀምሯል። ሚኒስትሯ፥ በዚህ ወቅት ብዝሃ ማንነቶቻችንና ዘመን ተሻጋሪ እሴቶቻችንን በመጠበቅና በማጎልበት ለአገር እድገትና የብልጽግና ጉዞ ማሳኪያ እንዲውሉ በትኩረት እየተሰራ ነው…

Read More

የአረንጓዴ ዐሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያና አሥተዳደር አዋጅ ጸደቀ

ኢትዮጵያ በደን ዘርፍ ከልማት አጋሮች የምታገኘውን ድጋፍና ጥቅም ለማሳደግ የሚያስችል የአረንጓዴ ዐሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያና አሥተዳደር አዋጅ ፀደቀ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 12ኛ መደበኛ ስብሰባ÷ የአረንጓዴ ዐሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አሥተዳደር አዋጅን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት አዋጁን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት÷ ዘላቂ ፈንድ ከማቋቋም…

Read More

ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ለሀገራዊ ምክክሩ ግብዓት የሚሆን አሻጋሪ ሃሳብ በማመንጨት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ተጠየቀ

ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ችግሮችን በዘላቂነት የሚፈቱና ለትውልድ የምትመች አገር ለመገንባት የሚያስችል አሻጋሪ ሃሳብ በማመንጨት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ። ” ተመካክረን ኢትዮጵያን እንገንባ፤ እኔም ለሀገሬ እመክራለሁ” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ባዘጋጀው መድረክ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ተዋቂ…

Read More

ባለፉት ሶስት ወራት አምራች ኢንዱስትሪዎች 816 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን ማምረት ችለዋል

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ባለፉት ሶስት ወራት አምራች ኢንዱስትሪዎች 816 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶች ማምረታቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ። የሀገር በቀል ኢኮኖሚ እና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ትግበራ ለአምራች ኢንዱስትሪው ያመጣው መልካም ዕድል፣ ተግዳሮት እና መፍትሔዎች ላይ ያተኮረ የመንግሥትና የግል ዘርፉ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤…

Read More

ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሹዌ ቢንግ ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት በሁኔታዎች የማይቀያየር ስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ ላይ መድረሱን በመግለጽ፤ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ለምታደርገው ጥረት የቻይናን ድጋፍ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም (FOCAC) የተቀመጡ ግቦችን ከአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ…

Read More

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ወደ ሰላማዊ መድረክ እንዲመጡ ጥሪ አቀረቡ

ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ፅንፈኝነት እና ግጭት ማንንም እንደማይጠቅም በመገንዘብ ወደሰላማዊ መድረክ እንዲመጡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ መንግሥት ሁልጊዜም ቢሆን ለሰላም በሩ ክፍት በመሆኑን አረጋግጠዋል። ዛሬ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች፣ የገጠር ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ህዝቡ ”ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ በነቂስ ወጥቶ ላሳየው…

Read More

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በአውሮፓውያኑ የ2025 አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ወራቶች በኢትዮጵያን እና ሶማሊያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ማቀዳቸው ተገልጿል፡፡ ጉብኝቱ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አደራዳሪነት ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ የታቀደ ነው ተብሏል፡፡ ባሳለፍነው ቅዳሜ ከቱርክ ወጣቶች ጋር ቆይታ የነበራቸው ፕሬዝዳንቱ፤ የአንካራው ስምምነት 7 ሰዓታትን የፈጀ እንደነበር በመግለፅ በሁለቱ ሀገራት ትብብር ከስምምነት መደረሱን ጠቁመዋል፡፡…

Read More