በካርዳችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን እውን ለማድረግ ዝግጁ ነን፡- የካፋ ዞን አርሶ አደሮች
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የመራጭነት ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን የካፋ ዞን አርሶ አደሮች ገልፀዋል። በዞኑ ጊምቦ ወረዳ የሾምባ ሼካ ቀበሌ አርሶ አደሮች እንደገለጹት የሚመራቸውን ዕጩ ለመምረጥ የሚያስላቸውን የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ለኢቢሲ ተናግረዋል። ያለፉት 6 ተከታታይ የምርጫ ሂደቶች ተሳትፈው የሚበጃቸውን የፖለቲካ ፓርቲ መርጠናል ያሉት አርሶ አደሮቹ የዘንድሮው ምርጫ ካለፉት ጊዜያት መሻሻሎች የታዩበት ነው…
