የቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል በአገር ውስጥ የተባዛ ቴትራ ኤች የተሰኘ የዶሮ ዝርያ እንቁላል በማስፈልፈል የመጀመሪያ ዙር የአንድ ቀን ጫጩቶችን ማሰራጨት ጀመረ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል ስራ አስኪያጅ አቶ ለገሠ ሻሮ እንደተናገሩት፣ማዕከሉ በምርታማነታቸው የተሻለ ውጤት የሚያስገኙ የዶሮ ዝርያዎችን በጥናት በመለየት የተጠቃሚውን ማህበረሰብ ፍላጐት የማሟላት ተግባር እያከናወነ ይገኛል። ለስጋና እንቁላል የሚሆኑ ቴትራ የተሰኙ ምርጥ የዶሮ ዝሪያዎችን ለክልሉ ሁሉም ዞኖች ለማሰራጨት በተደረገው የቅድመ ዝግጅት ስራ የክልሉ መንግሥት ወደ 60 ሚሊዮን ብር በጀት በመመደብ የማዕከሉን…
