Trendings

የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ ላይ የዞኑን ወቅታዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በመፈተሽ፣ የአመራሩን ቁመና የማጥራት ስራ ትኩረት እንደሚሰጠው ተገልጿል። በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ዋና አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ወንድሙ ኩርታ ዞኑ በክልል ደረጃ የተሻለ አፈፃፀም እያስመዘገበ ያለ ዞን መሆኑን ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠልና ህዝባዊ አገልጋይነትን ለማረጋገጥ አመራሩን በሦስት ዋና…

Read More

የኮሪደር ልማት ኢንሼቲቭ ከተማዋን ምቹ የስራ እና የመኖሪያ ማዕከል እያደረጋት ነው፦የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች

‎በከተማዋ እየተተገበረ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ የከተማዋን ገፅታ በእጅጉ የቀየረ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ነዋሪዎቹ ከተማ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ‎በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪ የሆኑት ኮማንደር ታረቀኝ ታፈሰ ከዚህ ቀደም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለረዥም ጊዜ በከተማዋ መኖራቸውን ጠቁመው አሁን እየተሰራ ያለ ኮሪደር ልማት ለመኖሪያ ምቹ መሆኑን ተናግረዋል። ‎በተለይ ዋናው መንገድ ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ ዜጎች…

Read More

ቆይታ ከእኛ ጋር!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክርቤት የግጭት አፈታት ስትራቴጂ ዙሪያ የተደረገ፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ስርዓት የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብትና እኩልነት መከበር ትኩረት የሰጠ ነው፡፡ በ1987 ዓ.ም የወጣው የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ-መንግሥት በርካታ የቡድን እና የግለሰቦች መብቶች እውቅና እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡ በዚህ ህገ-መንግሥት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በጋራ አብሮ ለመኖርና ለማድግ ያስችላቸው ዘንድ የግለሰብና የብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች መሠረታዊ መብቶች…

Read More

የአርብቶና አደርና ከፍል አርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል የግብይት ማዕከላትን ማጠናከርና ግብይት ሰንሰለቱን ማሳለጥ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነዉ።

የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አከባቢ ቢሮ ከአርብቶ አደር አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለንግድና ገበያ ልማት ባለድርሻ አካላት በሚዛን አማን ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። ‎በስልጠናዉ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አርብቶ አደርና ቆላማ አከባቢ ቢሮ ኃላፊ አቶ መቱ አኩ ቢሮው በአርብቶ አደር አካባቢዎች የተለያዩ አጋር አካላትን በማስተባበር መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማዳረስ ትኩረት…

Read More

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የካሳቫ ምርትን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ነዉ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የካሳቫ ምርትን ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ከመዋል ባለፈ፣ እሴት በመጨመር ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተቀናጀ ጥረት ሊደረግ እንደሚገባ ተጠቆመ። በኦሞ አዲስ አግሮ ፕላትፎርም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ በኢትዮጵያ ካሳቫ ኮንትራት አምራቾችና ኤክስፖርተሮች ማህበር እንዲሁም በኮመታ እርሻ ልማት ባለሀብቶች ማህበር ትብብር የተዘጋጀው ይህ ስልጠና፤ በካሳቫ አመራረት፣ በዘመናዊ እርሻና በአግሮ-ፕሮሰሲንግ ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ በሚዛን…

Read More

የዓለም የቡና ዋጋ በመቀነሱ አቅራቢዎች በእጃቸው ያለውን ምርት በፍጥነት ለገበያ እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀረበ

የዓለም የቡና ዋጋ በመቀነሱ አቅራቢዎች በእጃቸው ያለውን ምርት በፍጥነት ለገበያ እንዲያቀርቡ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አሳሰበ። ባለስልጣኑ ዓለም አቀፉን የቡና ገበያ ሁኔታና የኢትዮጵያን ቡና ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። ይህንን የዋጋ መዋዠቅ ተከትሎ፣ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ለቡና አቅራቢዎች፣ ላኪዎችና አርሶ አደሮች ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፈዋል። በተያዘው በጀት ዓመት ሀገሪቱ 1 ነጥብ 5…

Read More

ኮሌጁ የህበረሰብ ችግር ሊፈቱ በሚችሉ የስራ ዘርፎች ላይ ባለሙያዎችን በማደራጀት የስራ እድል እየፈጠረ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የታርጫ ፖሊ ቴክንክ ኮሌጅ ላለፉት በርካታ አመታት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን ተቀብሎ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በማሰልጠን ስራ ፈጣሪ ዜጎች እንዲበራከቱ እየሰራ ይገኛል። የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ኤፍሬም አይሳ ኮሌጁ አሁን ላይ አዲሱን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲን ተግባራዊ በማድረግ በኮሌጁ የሚሰጠውን ስልጠና ያጠናቀቁ ባለሙያዎችን የአከባቢውን ማህበረሰብ ችግር በሚፈቱ ዘርፎች በማደራጀት የስራ እድል እየፈጠረ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በኮሌጁ…

Read More

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 48ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 48ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል ፡፡ በዚህም መሠረት፦ 1ኛ.በክልሉ በተጨማሪነት እየተሰሩ ያሉ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ግንባታ ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ ገምግሟል።በዚህ በተጨማሪነት እየተሰሩ ያሉ አምስት የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በፍጥነት አልቀዉ ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ አቅጣጫ አስቀምጧል። 2ኛ. መስተዳድሩ ምክር ቤቱ…

Read More

የአመራር ምዘናው ጠንካራ ተቋም በመገንባት የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው፦ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በቦንጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የአመራር ግምገማና ምዘናው ከብልፅግና ፓርቲ ዕሳቤና መርሆዎች መነሻ ተቋማት የተጣለባቸውን የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በአመራር መሪነት የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር የሚገመግም እንደኾነ በመድረኩ ተገልጿል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በመድረኩ መክፈቻ ወቅት እንደገለጹት፥ የአመራር ምዘናው ጠንካራ ተቋም በመገንባት የህዝብ…

Read More

አርሶና አርብቶ አደሮችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ በማድረግ የመሬት አጠቃቀም ሥርዓት እንዲቀየርና የፋይናንስ አቅርቦት እንዲሻሻል በልዩ ትኩረት መሥራት ያስፈልጋል ፦አቶ ፍቅሬ አማን

የገጠር መሬት ባለይዞታዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ላይ ትኩረት ያደረገ የንቅናቄ መድረክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። መድረኩ ”ዲጂታል ማንነት ለተረጋገጠ የይዞታ ባለቤትነትና ለላቀ የፋይናንስ ተጠቃሚነት’ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ሲሆን ይህም የክልሉ ግብርና ቢሮ ከኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር በጋራ ትብብር ያዘጋጀው ነዉ። በመድረኩ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለጹት፣…

Read More