Trendings

በመንግሥት ከፍተኛ ድጎማ የሚቀርበውን ነዳጅ ከተተመነለት የዋጋ መጠንና የግብይት ሰንሰለት ውጪ በሚሸጡ ሕገወጦች ላይ የተጠናከረ እርምጃ መውስድ ተጀምሯል

በመንግሥት ከፍተኛ ድጎማ የሚቀርበውን ነዳጅ ከተተመነለት የዋጋ መጠንና የግብይት ሰንሰለት ውጪ በሚሸጡ ሕገወጦች ላይ የተጠናከረ እርምጃ መውስድ መጀመሩን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ አስታወቁ። የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ በነዳጅ አቅርቦት ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፤ መንግሥት በዓለም ተለዋዋጭ የገበያ ሁኔታ ውስጥ የህዝብን ጫና ለመቀነስ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ድጎማ እያደረገ ነው ብለዋል። በዚህም መንግሥት ነዳጅን ለኅብረተሰቡ ተደራሽ…

Read More

የህዝባችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ውጤት ተኮር አመራር እንገነባለን፦ አቶ ወንድሙ ኩርታ

በቤንች ሸኮ ዞን ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የፓርቲና የመንግስት ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ እና የአመራር ምዘና መድረክ በተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ መግባባት በመፍጠር በስኬት ተጠናቀቀ። በመድረኩ የዞኑ የግማሽ ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በአመራሮች መካከል ጥልቅ ውይይት ተካሂዷል። ባለፉት ስድስት ወራት በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ አዎንታዊ ውጤቶች እንዲቀጥሉ ጎልተው…

Read More

የቦንጋ ከተማ ለትውል ምቹ እንዲትሆን ወቅቱን የሚመጥን የከተማ ፕላን ያስፈልጋታል፦የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ

የቦንጋ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ላይ ያተኮረ የመረጃ ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የተገኙት የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ቦንጋ ከተማ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከተማ መሆኗን ተናግረዋል። ይህን የሚመጥን የከተማ መዋቅር በማስፈለጉ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ጋር ስምምነት ተደርጎ ወደ ትግበራ መገባቱንም ጠቁመዋል። የዛሬው መድረክ መረጃ የማሰባሰብ የመጀመሪያዉ ዙር መድረክ መሆኑን…

Read More

በትብብርና በፉክክር መሐል ሚዛን ማስጠበቅ ያስፈልገናል:- የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት “በትትብብርና በፉክክር መሐል ሚዛን እንጠብቃለን!” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ጉዳዮችና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካኸደ ነው። የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ግርማ ባሻ ለውይይት የሚሆን የቃል ኪዳን ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለጠንካራ ሀገረ መንግስትና ለዴሞክራሲ ግንባታ የሚያበረክቱት ሚና አይተኬ…

Read More

ዛሬውኑ የምርጫ ካርድዎን ይውሰዱ!

የሰባተኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 29/2018 ጀምሮ በይፋ ተጀምሯል። አገርን የመምራትና የወደፊት ዕጣ ፈንታን የመወሰን ስልጣን በሁላችንም እጅ ነው። ይህ ስልጣን በተግባር የሚገለጠው ደግሞ በምርጫ ሳጥን ውስጥ በሚቀመጥ አንድ ድምፅ ነው። ካርድ መውሰድ፡ የዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ የመጀመሪያው እርምጃ ምርጫ እንዲሳካና ድምፅዎ ዋጋ እንዲኖረው የመጀመሪያውና ወሳኙ ተግባር የምርጫ ካርድ መያዝ ነው። ካርድ ሳይኖር ድምፅ መስጠት አይቻልም፤…

Read More

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በመሶብ አገልግሎት ከ17 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ሆኑ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በሚዛን አማን ከተማ ስራ የጀመረው “የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት” ካለፈው ጥቅምት ወር ወዲህ ለ17 ሺህ 800 ዜጎች አገልግሎት መስጠቱን የክልሉ መሶብ አንድ ማዕከል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስራት አዳሮ አስታወቁ። ማዕከሉ የመንግስት አሰራርን በማዘመን ረገድ እያሳየ ስላለው ውጤት ማብራሪያ የሰጡት ዋና ስራ አስፈፃሚው፣ በአሁኑ ወቅት በአንድ ማዕከል ውስጥ አምስት የክልልና…

Read More

ታሪካዊ የባሕር በር መብታችንን ለማረጋገጥ የበኩላችንን እንወጣለን፡- ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሠራዊት ማኅበር

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሠራዊት ማኅበር ወቅታዊ በሆነው የሀገሪቱ የባሕር በር አጀንዳ ላይ የፓናል ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ላይ የማኅበሩ አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ብርሃኑ አማረ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር፤ የባሕር በር ጉዳይ ሀገራዊ አጀንዳ እንዲሆን በማድረጋቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል። “ኢትዮጵያና ቀይ ባሕር ተነጣጥለው አያውቁም” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በታሪክ አጋጣሚ…

Read More

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመማር ማስተማር ሂደት ተጎበኘ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያለውን የመማር ማስተማር እና የተግባር ማሰልጠኛ ክፍሎችን ጎብኝተዋል። ኮሌጁ ተማሪዎች ወደ ሥራ ከመሰማራታቸው በፊት በቂ ክህሎት እንዲጨብጡ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑ ተገልጿል። ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት የንድፈ-ሀሳብ ትምህርቱን ከተግባር ጋር ማቀናጀቱ ለጤናው ዘርፍ ዕድገት ወሳኝ መሆኑ ተመልክቷል። የመማር…

Read More

የኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ባለቤትነት ጥያቄ ለቀጣናዊ ሰላም ያለው ፋይዳ

ኢትዮጵያ በታሪካዊ አጋጣሚዎችና በሴራ ፖለቲካ ምክንያት አሁን የተገኘችበት የባሕር በር አልባነት ሁኔታ የብዙዎችን ትኩረት የሚስብ ጉዳይ ሆኗል። ይሁን እንጂ ታሪክ እንደሚመሰክረው ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር አካባቢ ገናና ስምና ዝና የነበራት ከመሆኑም ባለፈ የቀጣናው የንግድና የፀጥታ ባለቤት የነበረች ታላቅ ሀገር ነች። ኢትዮጵያ ቀደም ባሉት ዘመናት እስከ ባብ ኤል-መንደብ ድረስ ባለው ሰፊ ግዛት የባሕር ወንበዴዎችንና አሸባሪዎችን ሥርዓት በማስያዝ…

Read More

የሸካ ዞን የብልፅግና ፓርቲ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በቴፒ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

መድረኩ ከፓርቲው እሳቤና መርሆዎች ተነስቶ ተቋማት የተጣለባቸውን የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በአመራር መሪነት የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር የሚገመግም መሆኑ ተገልጿል። የግምገማ መድረኩን እየመሩ የሚገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ እንደገለጹት የመድረኩ ዋና ዓላማ የፓርቲውን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል እና የታዩ ክፍተቶችን በግልጽ በመወያየት የአመራሩን የመፈጸም አቅም ማሳደግ መሆኑን ገልጸዋል። የአመራር…

Read More