በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የፈተና አስተዳደርን በቴክኖሎጂ ለማዘመን ያለመ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ የፈተና ሥርዓትን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የመረጃ ትክክለኛነትን ለማረጋገጥና የፈተና አፈፃፀምን ለማሻሻል የሚያስችል የኦንላይን መዝጋቢዎች ስልጠና በቦንጋ ከተማ መስጠት ጀመረ። የክልሉ ትምህርት ቢሮ የ2017 እና 2018 የትምህርት ዘመናት የፈተና አፈፃፀም ግምገማና የስልጠና መርሃ ግብሩን በይፋ የከፈቱት የቢሮው ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ደስታ ገነሜ ናቸው። ዶክተር…
