Trendings

የኩታ ገጠም እርሻ፡ የዳውሮ ዞን አርሶ አደሮችን የልፋት ውጤት እያሳደገ ያለ ስራ

በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች፣ በተናጠል ከሚያካሂዱት እርሻ ወጥተው በኩታ ገጠም (ክላስተር) በመደራጀት የስንዴና ገብስ ምርታቸውን በእጅጉ ማሳደግ መቻላቸውን ተናገሩ። ይህ አዲስ የአሰራር ስርዓት፣ የባለሙያ ድጋፍን ከማቀለሉም በላይ እንደ አረም ያሉ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት በማስቻሉ “የልፋታችንን ዋጋ አግኝተንበታል” ሲሉ አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል ። በወረዳው ዳካ የሊ ቀበሌ በሚገኘው “ቦካ ክላስተር” እንደተስተዋለው፣ ቀደም…

Read More

የወጣቶች ስብዕና ማዕከላት የወጣቱን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነቱን በማረጋገጥ ጎላ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት ረቂቅ ስታንዳርድ ውይይት እና “ከማዘውተሪያነት ወደ ስብዕና ማበልጸጊያነት” የንቅናቄ መድረክ በሚዛን አማን ከተማ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት ረቂቅ ስታንዳርድ ውይይት እና “ከማዘውተሪያነት ወደ ስብዕና ማበልጸጊያነት” የንቅናቄ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን ሀገር ተረካቢ የሆኑ ወጣቱ ትውልድ ጊዜውን በአግባቡ መጠቀም እንዲችል…

Read More

በጤና ተቋማት በወሳኝ ኩነት ምዝገባ የተገኘውን ተሞክሮ በመውሰድ በባለቤትነት ወደ ሌሎች በማስፋት ለተሻለ አፈጻጸም መረባረብ ይገባል፦ አቶ በላይ ተሰማ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በቅንጅት በተሰሩ የ2017 በጀት ዓመት የተግባር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ አካሂደዋል። በውይይቱ ላይ በ2017 ዓ/ም በተፈጸሙ ተግባራት ዙሪያ የተደረገ የድጋፊና ክትትል ግብረ መልስ የተሞክሮ ቅመራ፣ ምዝገባ የጀመሩ የጤና ተቋማት የልደትና ሞት የ2017 ዓ/ም የኩነት አፈጻጸም ሪፖርት እና የአመያ መጀመሪያ…

Read More

የወሳኝ ኩነት መረጃ ስርዓትን ማጠናከርና ማዘመን ለሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ ሚናው የጎላ በመሆኑ የባለድርሻ አካላት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፦ አቶ በላይ ተሰማ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በቅንጅት በተሰሩ የ2017 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ እያካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የመንግሰት ረዳት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ እንደሀገር ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን አንስተው ለስኬቱ ቀጣይነት መረጃን ማዘመን ወሳኝ መሆኑን…

Read More

ከምንም ተነስተው ለከተማ ቤት ባለቤትነት የበቁት የ’አቦ’ ቡና አምራቾች የስኬት ታሪክ

በአንድ ወቅት መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ይቸገሩ የነበሩ የዳውሮ ዞን አርሶ አደሮች፣ ዛሬ በቡና ልማት ተደራጅተው ህይወታቸውን ከመቀየር አልፈው በከተማ ውስጥ ቤት እስከመግዛት የደረሰ የስኬት ጉዞ ላይ መሆናቸውን አስታወቁ። ይህ ታሪክ የመደራጀት ኃይልና የሥራ ትጋት ምን ያህል ለውጥ እንደሚያመጣ በተግባር ያሳየው የ”አቦ ቡና አምራቾች ህብረት ሥራ ማህበር” ነው። የስኬቱ መነሻ ታሪኩ የሚጀምረው 20 አርሶ አደሮች (10ሩ…

Read More

ከእጥፍ በላይ ምርት የሚሰጠው ‘መልካም’ የተሰኘው የማሽላ ዘር ለአርሶ አደሩ ሊቀርብ መሆኑ ተገለጸ

የቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል፣ የአካባቢውን አርሶ አደሮችና የክልሉን የማሽላ ዘር ፍላጎት ለማሟላት “መልካም” የተሰኘ ምርጥ የማሽላ ዘር እያባዛ መሆኑን አስታወቀ። ማዕከሉ በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በሚገኘው የኦትዋ ንዑስ ምርምር ጣቢያ እያካሄደው ባለው የዘር ብዜት፣ በሄክታር እስከ 60 ኩንታል የሚደርስ ምርት የሚሰጠውን ይህን ዝሪያ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ግብርና…

Read More

ቆይታ ከእኛ ጋር!

በክልሉ ባለፉት አምስት ወራት ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ከጊዜ ወደ ጊዜ የኢንቨስትመንት ፍሰት እየጨመረ ይገኛል። በተለይም ክልሉ ከተደራጀ በኋላ በዘርፉ ከፍተኛ ለውጥ ታይቷል። ይህም በአሃዝ ክልሉ ከመደራጀቱ በፊት የኢንቨስትመንት ፍሰት በአመት በአማካይ 25 ከመቶ ከነበረበት አሁን ላይ በአመት ወደ 105 ከፍ ማለት መቻሉም…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የቴሌቪዥን ስርጭት ፈቃድ አገኘ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመገናኛ ብዙሃን ተቋም የሆነው የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ፣ የህዝብ ብሮድካስት የቴሌቪዥን ስርጭት አገልግሎት ለመስጠት ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ይፋዊ ፈቃድ ዛሬ አግኝቷል። ይህ ፈቃድ የሚዲያ ተቋሙ የክልሉን ማህበረሰብ በተሟላ መረጃ ለማገልገል የጀመረውን ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ታሪካዊ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል። በዛሬው ዕለት በባለስልጣኑ ጽ/ቤት በተካሄደው የፈቃድ ርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ…

Read More

የተለያዩ የምርምር ቴክኖሎጂዎችን በማስፋት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ በሰፊ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል በቤንች ሸኮ ዞን ሼይ ቤንች ወረዳ ግብርና አካባቢ ጥብቃና ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር በስርዓተ ምግብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ አሲዳማ አፈር በኖራ በማከም በስንዴ ምርት ላይ በኩታ ገጠም አመራረት ዘዴን ማስተዋወቅና የማስፋት የአርሶ አደር መስክ ጉብኝት ፕሮግራም ተካሄደ። በሼይ ቤንች ወረዳ በመሃ ቀበሌ…

Read More

ከገጠር ትራንስፎርሜሽን ወደ ኢንዱስትራላይዜሽን ለሚደረገው ሽግግር የመንግስትና ግል ባንኮች ትብብርና ድጋፍ አጋዥ ነው፦አቶ ማስረሻ በላቸው

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢንዱስትሪ እና ኢኖቬሽን ቢሮ ከግልና መንግስት ባንኮች ጋር በመቀናጀት የኢንዱስትሪ ዘርፍ ውጤታማ ማድረግ በሚያስችል ጉዳዮች ዙሪያ በቦንጋ ከተማ እየተወያየ ነው። በውይይቱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፤ በክልሉ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል የመንግስት እና የግል ባንኮችን ያሳተፈ ካውንስል መቋቋሙን ተናግረዋል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን እውን በማድረግ…

Read More