የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የቴፒ ብዝሀ ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ ህብረት የመንግስት ሠራተኛ አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጀመረ
ስልጠናው “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል። ስልጠናው በመደመር መንግስት እይታ በግብርና መዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ፣የኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ፣የከተማ ልማት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፍ እመርታ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ያተኩራል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፀጋዬ ኃይሌ፣ ስልጠናው በአመራሩና በአባላት መካከል የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን መፍጠርን ዓላማ…
