Trendings

ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ በማድረግ ሁለተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ

በምዕራብ ኦሞ ዞን የዞኑ ሥራ ክህሎት መምሪያ የ2018በጀት አመት የ5 ወር እቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ምክክር እየተደረገ ይገኛል። በመድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ እንደተናገሩት ለወጣቶች ሥራ እድል ፈጠራ የተያዙ በጀቶች በአግባቡ እና በወቅቱ ማሰራጨት እንደሚገባ አስታውቋል። ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ በማድረግ ሁለተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪ አስገንዝበዋል። ለወጣቶች በገጠር እና በከተማ…

Read More

የመደመር መንግሥት የብዝሃ ኢኮኖሚ እሳቤ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ተወዳዳሪ አልሚዎችን እያፈራ ነው -ሚኒስትር መላኩ አለበል

የመደመር መንግሥት የብዝሃ ኢኮኖሚ እሳቤ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ተወዳዳሪ አልሚዎችን እያፈራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ለኢዜአ እንደገለጹት መንግሥት ለኢንዱስትሪ ልማት የሰጠው ትኩረት ዘርፉ በእጅጉ እንዲነቃቃና እመርታዊ ለውጥ እንዲያመጣ አስችሏል። ለአብነትም የፖሊሲ ለውጥ፣ የስትራቴጂ እና የተቋማትን ቅንጅታዊ አሰራር የሚያጠናክሩ የማሻሻያ ስራዎችን ጠቅሰዋል። በማሻሻያዎቹ በመታገዝ የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ለመጨመርና የአምራች ዘርፉን እድገት በቀጣይነት…

Read More

እንሰት፡ የአየር ንብረት ለውጥ የማይበግረዉ ሰብል

በዳውሮ ለም መሬት ላይ እንደ ሰንደቅ ዓላማ የሚውለበለበው የእንሰት ጫካ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ የጀርባ አጥንት ብቻ ሳይሆን የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የህይወት ዋስትናም ነው። ከስሩ እስከ ቅጠሉ እያንዳንዱ አካሉ ለተለያየ አገልግሎት የሚውለው ይህ የክልሉ ገጸ በረከት፣ ለአንድ የዳውሮ አባወራ የብርታቱ መገለጫና የሀብቱ ማሳያ ነው። ከባህላዊው ቆጮና ቡላ ጀምሮ እስከ ዘመናዊ ሆቴሎች ድረስ ተፈላጊነቱ ከፍ ያለ ነው።…

Read More

በክልሉ በቡና ማሣ ሽፋን ከ597 ሺህ 500 ሔክታር በላይ መድረሱን የክልሉ የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ባለሥልጣን አስታወቀ

‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቡና ልማት የተሸፈነው መሬት 597 ሺህ 521 ሔክታር መድረሱን የክልሉ የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አሥራት መኩሪያ ተናገሩ። ‎በክልሉ ለቡና ልማት ምቹ ሥነ-ምኅዳር መኖሩንና ካሉት 41 የገጠር ወረዳዎች በ38ቱ ቡና በስፋት እየለማ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ከወረዳዎቹ መካከል 26ቱ ቡናን ስፔሻላይዝድ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል። ‎በጫካ፣ በከፊል ጫካ፣ በጓሮ እና በዘመናዊ የተከላ…

Read More

በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ በመሠረተ-ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ የተመራው የአመራር ቡድን ከዳዉሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጋር የሦስት ወራት ግብ ስምምነት አካሄዱ

ከዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በቀጣይ ሥራዎች ዋና ዋና ግቦች ላይ የግብ ስምምነት ተደርጓል። በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ መሠረተ-ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ እንደገለፁት አመራሩ ከሕዝብና ከመንግሥት የተጣለበትን ኃላፊነት በጊዜ የለኝም መንፈስ በማከናወን የድርሻውን ሊወጣ ይገባል። ተግባራትን ቆጥሮ በመሥራት እንዲሁም በመፍጠር፤ በመፍጠን እና በዝላይ ዉጤት ማስመዝገብ መቻል እንደሚገባና…

Read More

የድጋፍና ክትትል ስራዎች ከስኬቶች ለመማር፣ ክፍተቶችን ለማረምና ተሞክሮዎችን ለመቀመር ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር በመሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል፦ አቶ ፍቅሬ አማን

የክልሉ የአመራር የድጋፍና ክትትል ቡድን በካፋ ዞን በፓርቲና በመንግሥት እየተከናወኑ ያሉት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ድጋፋዊ ክትትልና ምልከታ እያደረገ መሆኑ ይታወሳል። በዛሬው ዕለት የአመራር ቡድኑ በካፋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በ90 ቀናት በፓርቲና በመንግስት የተቀመጡ ዕቅዶችን ለማሳለጥ እየተደረገ ያለውን የድጋፍ፣ ክትትልና የምልከታ ስራዎችን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገምግመዋል። በድጋፍና ክትትል ስራዎች በ90…

Read More

የሾኬላ ዋሻና ፏፏቴ – ድብቁ የቱሪዝም ሀብት

የሾከላ ዋሻና ፏፏቴ የሚገኘው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በኮንታ ዞን፣ አመያ ዙሪያ ወረዳ በኦፓ ላሼ ቀበሌ ውስጥ ነው። የዋሻው አጠቃላይ ይዘት እና ስፋት በዞኑ ውስጥ ካሉት ሌሎች ዋሻዎች ቀዳሚውን ደረጃ የሚይዝ እንደኾነም ነው የሚገለጸው። ሾከላ የሚለውን የዋሻው ስያሜ የተገኘው፥ ከዋሻው አናት ላይ በግምት ከ50 ሜትር በላይ ርቀት ወደታች የሚወረወረው ሾኬላ በተባለው ፏፏቴ ስም እንደተሰየመም ከዞኑ ባህል…

Read More

በመደመር መንግስት ዕይታ የዘርፎች እመርታ ስልጠና ላይ በተገኘው ክህሎት አመራሩ በአግባቡ በመጠቀም እቅዶች ማሳካት እንደሚገባ ተገለፀ።

በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ በአቶ ነጋ አበራ የተመራው የድጋፍ እና ክትትል ቡድን ከምዕራብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በቀጣይ ሥራዎች እቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል። በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንደተናገሩት አመራሩ በመፈጠር፤ በመፍጠን እና በዝላይ ዉጤት በሚመጣ መንገድ እና አማራጮች…

Read More

በሥልጠናው የተቀመጡ ሀገራዊ የብልጽግና ግቦችን ለማሳካት የአመራር ቁርጠኝነት ፣ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ዝላይ መርሆዎችን መከተል ከሁሉም ይጠበቃል፦አቶ እንዳሻው ከበደ

“በመደመር መንግሥት እይታ፤የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሃሳብ ሲሰጥ የቆየው የካፋ ዞን 3ኛ ዙር አመራሮች ስልጠና በስኬት ተጠናቋል ። የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ አጠቃላይ የሥልጠና ቆይታ አስመልክቶ ማጠቃለያና ቀጣይ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል:: አመራሩ የተያዙ የብልጽግና ግቦችን ለማሳካት በጠንካራ የአመራር ቁርጠኝነት፣ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ዝላይ መርሆዎችን ተከትሎ በመስራት ፈጣን ለውጥ ማስመዝገብ ይጠበቅበታል ብለዋል ። ከስልጠና…

Read More

አመራሩ የልማት አቅሞችን በመጠቀምና ከህብረተሰቡ ጋር ተግባቦት በመፍጠር በቀጣይ አጭር ጊዜያት ውስጥ የሚታዩ ተጨባጭ ውጤቶች ለማስመዝገብ መስራት ይገባል፤ አቶ ታከለ ተስፉ

በኮንታ ዞን ላለፉት 9 ቀናት “በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ቃል ለ3ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና እየተጠቃለለ ይገኛል። በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ እንደ ሀገር የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን በአመራሩ ዘንድ የአመለካከትና የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠር ተቀዳሚ ተግባር ስለመሆኑ አስረድተዋል። ከዚህ መነሻ በሀገር አቀፍ…

Read More