በካፋ ዞን የተለያዩ ከተማ አስተዳደሮች “የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ የኢትዮጵያን ማንሰራራይ እውን እናደርጋለን!” በሚል መሪ ሃሳብ ከነዋሪዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።
መድረኮቹ በሁሉም ዘርፎች የተመዘገበዉን ለዉጥ በማስቀጠል የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቅነት በመፍታት የህዝቡን ተጠቃሚነት በሁሉም ዘርፍ ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነው። የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ውይይቱን የመሩት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ መጠነ ሰፊ ተግባር መከናወኑን ገልጾ በዚህም ለህዝብ ድምፅ ትኩረት በመስጠት ማዘጋጃ ቤት ላይ ያደረገው የሪፎርም ስራና 13…
