ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ኢትዮጵያውያን የሀገርን ዳር ድንበር እና ክብሯን ለማሰጠበቅ የደም ዋጋ የከፈሉበት የነፃነት ዓርማችን ነው ፦ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ
“ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት ፣ብሔራዊ አንድነታችን፣ሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ”በምል መሪ ቃል ለ18ተኛ ዙር በዞን ማዕከል ታርጫ ከተማ በድምቀት ተከብሯል። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ኢትዮጵያውያን የሀገር ዳር ድንበር እና ክብሩዋን ለማስጠበቅ የደም ዋጋ የተከፈለበት የነፃነት ዓርማችን ነው ብለዋል። አክለውም…
