Trendings

ለሁለት ተከታታይ ቀናት በቴፒ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክርቤት 1ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ ።

ምክርቤቱ በዛሬው ውሎ የምክርቤቱ አባላት የአሰራርና የአባላት ሥነሥርዓት ለመደንገግ በወጣ ደንብ ላይ መክሯል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የብሔረሰቦች ምክርቤት የአሰራርና የአባላት ሥነሥርዓት ለመደንገግ የወጣ ደንብ በአቶ መቱ አኩ ቀርቧል። የክልሉን ብሔረሰቦች ምክርቤት ሥልጣን እና ተግባርን ለመዘርዘር በወጣው አዋጅ ቁጥር 10/2014 አንቀጽ 43 መሠረት በማድረግ ደንቡ መዘጋጀቱን አቶ መቱ አኩ ገልጸዋል ። የተዘጋጀው ደንብ…

Read More

7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ውጤታማ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡ የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

የምርጫ ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የበኩላቸውን ድርሻ ከመወጣት በተጨማሪ የተሰጣቸውን የመምረጥ ዕድል በአግባቡ እንደሚጠቀሙም ያነጋገርናቸው የከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ለ7ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ የሚሳተፉት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊና ፍትሐዊ እንዲሆን ለማስቻል ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም የታርጫ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ በለጠ ባሹ ገልፀዋል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሃዊ ሰላማዊ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ሁላችንም ኃላፊነት መውሰድ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነዳጅን በኃላፊነትና በቁጠባ እንድንጠቀም አሳሰቡ

በመካከላኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነደጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት ተቸግረዋል። በመሆኑም ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል። በመሆኑም የነዳጅ አከፋፋዮች፣ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ፣ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በሃላፊነት ስሜት እንድንጠቀም ለማሳሰብ እወዳለው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

Read More

የልማት ተደራሽነትና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በለውጡ የተመዘገበ ትልቅ ድል ነው፦አቶ ፍቅሬ አማን

የመጋቢት 24 ታሪካዊ ቀን በሚዛን አማን ከተማ በድምቀትና በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጺያ ህዝቦች ከልልመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን በድጋፍ ሰልፉ ላይ ለውጡ ያመጣቸው ዋና ዋና ድሎች መካከል የልማት ተደራሽነትና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት መሆኑን ጠቅሰው የህዝብ የራስን ራስ አስተዳደር ጥያቄ በተግባር መረጋገጡን ገልጸዋል። በክልሉ የተጀመረው የኮሪደር ልማትና የአንድ መሶብ አገልግሎቶች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት…

Read More

የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተግባር የተደገ ሥራ ይጠበቃል:-አቶ አልማው ዘውዴ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የማህበራዊ ክላስተር ተቋማት የ2016 በጀት አመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተግባር የተደገፈ ቅንጅታዊ አሰራርን መከተል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የግምገማ መድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ጠንካራ አፈፃፀሞችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በጉድለት የተገመገሙ…

Read More

በትብብርና በፉክክር መሐል ሚዛን ማስጠበቅ ያስፈልገናል:- የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት “በትትብብርና በፉክክር መሐል ሚዛን እንጠብቃለን!” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ጉዳዮችና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካኸደ ነው። የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ግርማ ባሻ ለውይይት የሚሆን የቃል ኪዳን ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለጠንካራ ሀገረ መንግስትና ለዴሞክራሲ ግንባታ የሚያበረክቱት ሚና አይተኬ…

Read More

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት የሚዘክር ደማቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በተገኙበት በቦንጋ ከተማ ደማቅ የድጋፍ ስልፍ እየተካሄደ ይገኛል። በሀገራዊ ለውጡ ለተገኘው አንጸባራቂ ድል እውቅና በሚሰጠው በዚህ የድጋፍ ሰልፍ የመጋቢት 24 ትሩፋቶችን የሚዘክሩ የተለያዩ መልዕክት በሰልፈኞች እየተላለፉ ይገኛል። በህዝባዊ ትዕይንቱ የቦንጋ ከተማ እና ከዞኑ ሁሉም…

Read More

ከ451 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

ባለፉት 6 ወራት ከ451 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማውን በቢሾፍቱ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ ሚኒስትሯ ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ÷ በተያዘው በጀት አመት ተቋሙ በ”ግብር ለሀገር ክብር “ንቅናቄ ከቢሊየን ወደ ትሪሊየን ገቢ ስኬት የሚያደርገው ጉዞ ስኬታማ እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል። በተያዘው በጀት አመት 6 ወራትም 445 ነጥብ 8 ቢሊየን…

Read More

ባለፉት ዓመታት 249 ሺህ ቤቶች ለአቅመ ደካማ ዜጎች ተላልፈዋል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

መንግስት ባለሐብቶችን በማስተባበር ባከናወነው ስራ ባለፉት ዓመታት 249 ሺህ ቤቶችን በመስራት እና በማደስ ለአቅመ ደካማ ዜጎች መተላለፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለአቅመ ደካማ ዜጎች ቤት ሰርቶ መስጠት ልምምድ ያደረገ የግል ባለሐብት እየተፈጠረ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህ ተግባር ውስጥ የተሳተፉ ባለሐብቶች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል። የኑሮ ውድነቱ እጅ አጠር ዜጎች ላይ ጫና…

Read More

የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የመረጃ ሥርዓት የዘመነ የህብረተሰቡን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆን ይገባዋል፦ አቶ ታከለ ታምሩ።

በካፋ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አመቻችነት በዞኑ የሚገኙ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች የመረጃ ሥርዓት ከማዘመን አኳያ በሚታዩ ተግዳሮቶችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የጋራ ውይይትና ምክክር መድረክ አካሂዷል ፡፡ የካፋ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ታከለ ታምሩ በመክፈቻ ንግግራቸው የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተቋማት የመረጃ ሥርዓት የዘመነ፣ ችግር ፈቺና የህብረተሰቡን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆን ይገባቸዋል…

Read More