Trendings

ዜጎች ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት የጋራ እሴቶችን ማጠናከር ተገቢ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክርቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ አሳሰቡ

ለ18ኛ ጊዜ ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመይ ብስራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነትና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ በሚል መሪ ቃል በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ተከብሯል ። በክልሉ ታርጫ ከተማ የተገኙ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አቶ ወንድሙ ኩርታ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ነፃነቷን ከማስከበር ባለፈ ለሌሎች ነፃነታቸውን ለተነጠቁ የአፍሪካ አገራት ነፃነት ፈንጣቂ አገር በመሆን የድርሻዋን ተወጥታለች። ከዚህ የተነሣ በኢትዮጵያ በጀብዱነትና…

Read More

ርዕሠ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እንኳን ለፍቼ ጫምባላላ ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሠ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ‹‹ ፍቼ ጫምባላላ ›› የአብሮነት ፣የአንድነትና የሰላም ተምሳሌት የህዝቦችን የእርስ በርስ መስተጋብር የሚያጠናክር የሲዳማ ብሔር ድንቅ እሴት ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት የሲዳማ ህዝብ ያቆየው በዓለም በማይዳሰሱ ቅርስ የተመዘገበ የኢትዮጵያ ብቻ የዓለም በዓል ጭምር…

Read More

የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተግባር የተደገ ሥራ ይጠበቃል:-አቶ አልማው ዘውዴ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የማህበራዊ ክላስተር ተቋማት የ2016 በጀት አመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተግባር የተደገፈ ቅንጅታዊ አሰራርን መከተል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የግምገማ መድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ጠንካራ አፈፃፀሞችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በጉድለት የተገመገሙ…

Read More

ኢትዮጵያ ማንሠራራት በጀመረችበት እና ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በተመረቀበት ጊዜ ለሚከበረው አዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ማንሠራራት በጀመረችበት እና ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በተመረቀበት ጊዜ ለሚከበረው አዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያለፈው ዓመት ፈጣሪ ከጎናችን፣ ስኬት በደጃችን መሆኑን ያየንበት ዓመት ነበር፡፡ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ በአምራችነት እና በአይሲቲ ዘርፎች ያስመዘገብናቸው ውጤቶች ይሄንን ይመሰክራሉ፡፡ ኢትዮጵያን ያህል ሀገር፣ ኢትዮጵያውያንን ያህል ሕዝብ ይዘን በትጋት ከሠራን፣ ከዚህ በላይ ድል ልናሳካ እንደምንችል…

Read More

ኮሚሽኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አጀንዳዎችን ተረከበ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሰባት ክፍሎችና በ64 ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ያዘጋጃቸውን አጀንዳዎች መረከቡን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ አጀንዳዎቹን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ከሌሎች ኮሚሽነሮች ጋር በጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ ከተመራው የምክር ቤቱ የሥራ አስፈፃሚ አባላት ቡድን መረከባቸው ተገልጿል፡፡ መስፍን (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት ኮሚሽኑ ከምክር ቤቱ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሞ…

Read More

ከመስከረም ጀምሮ ለሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወሰነ

ከመስከረም ጀምሮ ለሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወሰነ ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ ነው ብሏል፡፡ በዚህም ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑን አስታውቋል፡፡ በማሻሻያው ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4…

Read More

“ዛሬ በናይሮቢ፣ ኬንያ “ዲጂታላይዜሽንን ለቀጠናዊ የእሴት ሰንሰለት መጎልበት በመጠቀም ለዘላቂ እና አካታች እድገት ማዋል” በሚል ጭብጥ በተካሄደው 24ኛው የCOMESA መሪዎች ጉባኤ ላይ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የአፍሪካን የኢኮኖሚ ታሪክ የመቀየር ልዩ እድል እንዳቀረበልን አፅንኦት ሰጥቼ አንስቻለሁ።

እንደ አኅጉር የየሀገሮቻችንን ጥረቶች ለማጣመር እና ቀጠናዊ ትስስሮችን ለማፋጠን ክሂሎቱ እና መሠረቱ አለን። በኢትዮጵያ ዲጂታል ክሂሎትን ለማበልጸግ እና አስፈላጊ መሠረተ ልማት ለመገንባት ጥሩ ርምጃዎች ተራምደናል። የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ነን።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ

Read More