Trendings

ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ የሚመራው በረራ ዛሬ ማታ ወደ ለንደን ጋትዊክ ያቀናል::

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በየአመቱ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ የሚመራው በረራ ዛሬ ማታ ወደ እንግሊዝ ሀገር ለንደን ጋትዊክ ያቀናል:: ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ማርች 8 አስመልክቶ በአየር መንገዱ በሴቶች ብቻ የሚመራ ጉዞ ወደተለያዩ መዳረሻዎች የሚበር ሲሆን ዘንድሮም ለ9ኛ ጊዜ “ሴቶችን በማብቃት አፍሪካን ማስተሳሰር” በሚል መሪ ቃል ወደ ለንደን ለሚጓዙ የሴት ልዑካን…

Read More

የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ትግበራው የወጪ ንግድና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታና ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ ነው

የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ትግበራው የወጪ ንግድና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታና ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ መሆኑን የሞሃን ኩባንያ ሊቀ-መንበር እና የህንድ ቢዝነስ ፎረም ሊቀመንበር ማዩር ኮታሪ ተናገሩ። በኢትዮጵያ በተለያዩ የማምረቻ ዘርፎች ላይ የተሰማራው የሞሃን ኩባንያ ሊቀ-መንበር እና የህንድ ቢዝነስ ፎረም ሊቀመንበር ማዩር ኮታሪ፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ትግበራውን በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በፖሊሲ ተግበራው በመንግስት የተወሰደው እርምጃ ብዙዎች ሲጠብቁት የነበረ…

Read More

የባህር በርን በተመለከተ የሚነሳው ጥያቄ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል – ምሁራን

የባህር በር ጉዳይን በተመለከተ የሚነሳው ጥያቄ ሳይቀዘቅዝ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ሲሉ ምሁራን ገልጸዋል። የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪ ጌትዬ ትርፌ መንግስት የባህር በር ጥያቄን አጀንዳ አድርጎ ባቀረበበት ወቅት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የመገናኛ ብዙኃን ትልቅ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመው÷ አሁን ላይ ግን እየቀነሰ መምጣቱን ተናግረዋል። አጀንዳውን በተመለከተ የሚነሳው ጥያቄ ሳይቀዘቅዝ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ አንስተው÷ የባህር በር ጥያቄው…

Read More

የዳኝነት አገልግሎትን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት አስፈላጊ ነው:- የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ 2018 ግማሽ ዓመት የፍርድ ቤቶች አፈጻጸም ላይ ከተገልጋይ፣ ከህዝብና ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ እያካኸደ ነው። በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግግር ያደረጉት የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ከታችኞቹ ተቋማት የጀመረው ይህ መድረክ በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ግብዓት መሰብሰብ የሚያስችል ወሳኝ…

Read More

ለቡና ምርት፣ምርታማነትና ጥራት መረጋገጥ ከቡና ዘር ዝግጅት ጀምሮ በልዩ ትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ

ለቡና ምርት፣ምርታማነትና ጥራት መረጋገጥ ከቡና ዘር ዝግጅት ጀምሮ በልዩ ትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ የክልሉ ቡና፣ሻይና፣ቅመማቅመም ባለስልጣን አመላከተ የክልሉ ቡና፣ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን በቡና ዘር አዘገጃጀት ላይ ለዞን፣ወረዳ፣ቀበሌ ባለሙያዎች እና ለቡና ዘር አዘጋጅ አርሶ አደሮች የተግባር ተኮር የአሰልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ነዉ። ስልጠናው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ቡና፣ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን ከክልሉ ‎ግብርና ቢሮ የምግብ ሥርዓት…

Read More
Camera: Akilelu Beyene

በቡና ምርት የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ በብዛትና በጥራት ማምረት እንደሚገባ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን “የቡና ምርት ጥራት ለጋራ ብልጽግናችን” በሚል ቃል የንቅናቄ መድረክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ አካሂዷል ፡፡ የቡናን ምርት በብዛት እና በጥራት በማምረት ሀገሪቱን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠብቅ ተገልጿል። የንቅናቄው መድረክ ተሳታፊዎች በአርሶአደሩ ላይ የሚስተዋለውን የቡና ግብይት ስርዓትን ማዘመንና ህገ ወጥ የቡና…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች 18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አከበሩ፤ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በተገኙበት “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ’ በሚል መሪ ሃሳብ አክብረዋል።

Read More

በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተላለፉ ውሳኔዎችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በመፈፀም የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ።

በምዕራብ ኦሞ ዞን በጀሙ ከተማ “ከቃል እስከ ባህል!” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው 2ኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ወሳኔ እና አቅጣጫዎች ላይ ከከተማ ማህበረሰብ ጋር ዉይይት እየተደረገ ይገኛል። በመድረኩ የክልሉ የአካባቢው እና ደን ጥበቃ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አስራት ገብረማርያም እንደተናገሩት ብልጽግና ፓርታ በባለፉት አመታት በርካታ ሥራዎች ሰርቷል ብልዋል። ዶክተር አስራት በ2ኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ላይ…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፖሊስ የማርሽ ባንድ ምልምል ሰልጣኞች ስልጠናቸውን ጀመሩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፖሊስ የማርሽ ባንድ ምልምል ሰልጣኞች ስልጠናቸውን ጀመሩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያቋቁመውን የፖሊስ ማርሽ ባንድ አባላትን ለማደራጀት ከሁሉም የክልሉ ዞኖች የተመለመሉ ወጣቶች ወደ ስልጠና ገብተዋል። ሰልጣኞቹ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አቦስቶ ካምፓስ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ ስልጠናቸውንም በላቀ የፖሊሳዊ ሥነ-ምግባር እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። በአቀባበል ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ…

Read More