Trendings

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከአሜሪካው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው የአሜሪካውን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳውን ተቀብለው አነጋግረዋል። በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል፡፡ በተጨማሪም በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ የሐሳብ ልውውጥ አድርገዋል። ኢትዮጵያና አሜሪካ ለ120 ዓመታት የዘለቀ ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ የዛሬው ውይይትም…

Read More

ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው የኢኮኖሚ ዕድገት ለሌሎች አርአያ መሆን እንደሚችል ፓኪስታን ገለጸች

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር የውጭ ግንኙነት ልዩ አማካሪ ሰይድ ታሪቅ ፋጢሚ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሀገራቱ ሰላም፣ ብልጽግና እና የዘላቂ ልማት የጋራ ግቦችን ለማሳካት የባለብዙ ወገን ትብብርን ጨምሮ በጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ ሁለቱ ወገኖች በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ አቪዬሽን፣ ቴክኖሎጂና አየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። አምባሳደር…

Read More

በቱርክ ሲደረግ የነበረው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር በስምምነት ተጠናቀቀ

በቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት በአንካራ ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር ሁለቱንም አገራት በሚያግባባ ስምምነት ተጠናቅቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ግብዣ ዛሬ ምሽት በአንካራ ውይይት አድርገዋል፡፡ ሁለቱ መሪዎች ውይይቱን ካደረጉ በኋላም በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። መሪዎቹ በመግለጫቸውም፤ ኢትዮጵያ በሶማሊያ የባሕር ዳርቻ…

Read More

የህልም ጉልበት፣ ለእመርታዊ እድገት ” በሚል መሪ ቃል በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ላለፉት አስር ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው 3ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ በስኬት ተጠናቋል።

በማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ለአመራሩ የሥራ መመሪያ የሰጡት የዳውሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ እንደገለፁት የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥና የኅብረተሰቡን ህይወት ለማሻሻል የአመራሩ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው። ህልማችንን ለማሳካት በተገቢው መተለምና የወል ትርክትን በማፅናት እንዲሁም መተግባር ከምንም ጊዜ በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነውም ብለዋል። ከስልጠናው ማግስት ጀምሮ በንድፈ ሃሳብና በመስክ ጉብኝት…

Read More

ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በግብርና፤ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አረጋገጡ

ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በግብርና፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ አማራጮችን በመጠቀም ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ። ከሁለተኛ የምግብ ስርዓት ጉባኤ ጎን ለጎን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የአካባቢና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር አምና አልደሃክ (ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገዋል። ሚኒስትሮቹ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ጠንካራና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት በውይይታቸው አንስተዋል። የኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስትር ግርማ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢንዱስትሪ ዘርፍን በተመለከተ የሰጡት ምላሽና ማብራሪያ:-

በኢንዱስትሪው ዘርፍ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ መንግስት ጣልቃ በመግባት የኢኮኖሚ መሻሻያ አድርጓል፤ በዚህም ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል፣ የሀይል አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በተከናወኑ ተግባራት በዘርፍ ኢነርጂ 100 ፐርሰንት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፣ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር በኢንዱስትሪው ዘርፍ 50 በመቶ የሀይል አቅርቦት ጭማሪ ተደርጓል፣ ከግብዓት ጋር እንዲሁም ከኢንዱስትሪ መሬት አቅርቦት ጋር በተያያዘ መንግስት በርካታ ስራዎችን አከናውኗል፣ ኢትዮጵያ…

Read More

ከ94 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በቦንጋ ከተማ እየተገነባ ያለው የመናኸሪያ ግንባታ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተጠቆመ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ እየተገነባ ያለው የመናኸሪያ ግንባታ ነሐሴ 21 ቀን 20/14 በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ መሠረተ ድንጋይ ተቀምጦለት ወደ ስራ መገባቱ ይታወቃል፡፡ ይህ ከክልሉ መንግስት በተመደበ በ94 ነጥብ 1ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ በጆስ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል ድርጅት እየተገነባ ያለው ዘመናዊ መናኸሪያ ሲሆን ከ11 ሺህ…

Read More

#ሪፖርታዥ

የመማር ማስተማር ሥራን ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ  ትምህርታዊ ኢንሼቲቮች ተቀርጸው ተግባራዊ እየሆኑ ነዉ ፦የክልሉ ትምህርት ቢሮ በክልሉ የመማር ማስተማር ሥራን ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ የተለያዩ ትምህርታዊ ኢንሼቲቮች ተቀርጸዉ እየተተገበሩ እንደሚገኙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ ገለጸ። የመማር ማስተማር ሥራን ውጤታማ ለማድረግ ተቀርጸዉ እየተተገበሩ ከሚገኙ ሂደታዊ ከሆኑ ከተለያዩ ኢንሼቲቮች ወይም ትምህርታዊ ፕሮግራሞች አንዱ የትምህርት ቤት…

Read More

በአቪዬሽን አሰራር ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ “ዳዊት ድሪባ በዳኔ” በሚል ስም የ3 ጊዜ የሞት ፍርደኛ እንደነበር ፖሊስ አስታወቀ

ሰሞኑን በአቪዬሽን አሰራር ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ፣ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ “ዳዊት ድሪባ በዳኔ” በሚል ስም 3 ጊዜ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት እንደነበር ፖሊስ ገልጿል፡፡ ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ እንደተቻለው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ታሕሳስ 25 ቀን 1999…

Read More