ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ ከ280 በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አነስተኛ መስኖ መርቀው ከፍቱ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)÷ በዳውሮ ዞን፣ ማረቃ ወረዳ በክልሉ የመስኖ ኤጄንሲ የተሰራውን የውኒ አነስተኛ መስኖ መርቀው ከፍተዋል። ከ144 ሄክታር የማልማት አቅም ያለው የመስኖ ፕሮጀክት የተገነባው ከ75 ሚሊዮን በሚጠጋ የክልል መንግሥት የበጀት ድጋፍ ነው። ፕሮጀክቱ የ5.7 ኪሎሜትር ዋና የውሃ ካናል የመስመር ዝርጋታ እና ሌሎች የስትራክቸርና መካኒካል ሥራዎች ያካተተ ሲሆን…
