ሚኒስቴሩ ከቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን ጋር በትብብር ለመስራት ተፈራረመ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን ጋር በተለያዩ መስኮች በትብብር መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱ በ2ኛው ምዕራፍ የትብብር ማዕቀፍ በ7 ዋና ዋና የልማት መስኮች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያና ቻይና በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፍ ለዓመታት የዘለቀ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዋል።…
