በመንግስት እየተመቻቸ የሚገኘዉን የዉጭ ሀገር የስራ ስምሪት እድል ህብረተሰቡ በአግባቡ ሊጠቀም እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ጥሪ አቀረበ።
ይህም በህገ-ወጥ መንገድ ለስራ ፍለጋ ከሀገር የሚወጡ ዜጎች ላይ የሚደርሰዉን በደሎችና የመብት ጠሰቶችን ጥሰቶች የሚስያቀር መሆኑም ተጠቁሟል። የዉጭ ሀገር የስራ ስምሪት መንግስት ሰራተኛ ከሚፈልጉ ሀገራት ጋር ህጋዊ ስምምነት በመፈፀም ክህሎት ያላቸዉ ዜጎች ደንነታቸዉ ተጠብቆ ወደ ዉጭ ሀገር በመሄድ የስራ ዕድል የሚጠቀሙበት አሰራር መሆኑን የቢሮዉ ምክትል ሀላፊና የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ሀላፊ ዶክተር ተክለአብ ቡሎ ተናግረዋል። ይህም…
