Trendings

በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ ዲጂታል ማንነት ተስፋ ሰጪ ከሆነው ፈጠራ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሠረታዊ ምሦሶ ተሻሽሏል። ከአሁን በኋላ አማራጭ ሳይሆን ሰዎችን ከአገልግሎቶች፣ ከማኅበረሰቦች፣ ከተቋማት እና ከመንግሥታት ጋር የሚያገናኝ አስፈላጊ መሠረተ ልማት ነው።

ከአምስት ዓመት በፊት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ራዕይ እየተመራን እጅግ አስፈላጊ ውሳኔ ወስነናል። ይህም ዘመናዊ፣ አካታች፣ መሠረት ያለው እና ሊሰፋ የሚችል ዲጂታል የማንነት ሥርዓት መገንባት ነው። ይሄንንም ለእያንዳንዱ ነዋሪ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ነበር። ይሄንን ሥርዓት ‘ፋይዳ’ ብለን እንጠራዋለን። ፋይዳ ካርድ ብቻ አይደለም። የግለሰቦችን ግላዊ መረጃዎች ምሥጢራዊነት በመጠበቅ እና አስፈላጊ የሆነውን ብቻ በማጋራት ማንነትዎን የሚያረጋግጥ ልዩ መለያ…

Read More

የአመራር ውጤታማነትን በየደረጃው ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት አስታወቀ።

በየደረጃው ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ችግር ፈቺ ምላሽ ከመስጠት አንጻር የሚስተዋለውን ክፍተት ለማረም የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት እንደተሰጠባቸው ፓርቲው አመላክቷል ። የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ልዩ አማካሪ አቶ አለማየሁ አይበራ የመንግስትን እና የፓርቲ ስራዎች የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሥራ ዘመን ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳመላከቱት ተልዕኮውን በብቃት መምራት የሚችል…

Read More

የግብርና ፍኖተ ካርታ በግብርናው ዘርፍ የሚታዩ ማነቆዎችን የሚፈታ ነው።

ግብርና የህብረተሰቡ ኑሮ መሠረትና የኢኮኖሚ ዘርፍ ትልቅ አቅም ነው :: ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር እና በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ትብብር የተዘጋጀ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የግብርና ፍኖተ ካርታ ጥናት ሰነድ ርክክብ ተደርጓል ። በጥናት ሰነዱ ርክክብ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ግብርና…

Read More

በጎነትን ለማስረጽ እና የአብሮነት እሴቶችን ለማጎልበት የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ ገለፁ።

የ2016 የወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልገሎት ተሳታፊዎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተለያዩ በጎ ተግባራትን አከናውነዋል ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ እንደገለፁት ወሰን ተሻጋሪ የክረምት ወራት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ሠላምን አስተማማኝና ዘላቂ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ ሚናቸው የጎላ ነው…

Read More

የማርበርግ ቫይረስን በመከላከልና መቆጣጠር ረገድ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ነው – ኢብራሂም ተማም

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ፣ ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የማርበርግ ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ ለጤና ባለሙያዎች በቦንጋ እና ሚዛን ከተሞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። ቢሮው በመጀመሪያ ዙር ከክልሉ ሁሉም ዞኖች ለተወጣጡ 3መቶ 29 የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች እና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በበሽታው መተላለፊያ፣ መከላከያ እና መቆጣጠር እንዲሁም በበሽታው ምንነት ዙሪያ የተዘጋጀውን ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።…

Read More

በሸገር ከተማ አስተዳደር በከባድ የማታለል ወንጀል ሲፈለግ የነበረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኝኙነትና ኮሚንኬሽን ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ በሸገር ከተማ አስተዳደር በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ በተለያዬ አራት ሀሰተኛ ስሞችን በመጠቀም በ15 ግለሰቦች ላይ በከባድ የማታለል ወንጀሎች በመፈፀም ክስ ተመስርቶበት በፖሊስ ሲፈለግ መቆየቱን ፖሊስ ኮሚሽኑ ገልጿል። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ተጠርጣሪውን በተገኘበት እንዲያዝ ከፍርድ ቤት መያዣ ጋር በመላካቸው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ…

Read More

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች እየተከበረ ይገኛል። ዘንድሮ ቀኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳድሮች በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ እንደሚገኝ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Read More

በልማት ወደኋላ ለቀሩና ለተዘነጉ አካባቢዎች የብልፅግና ፓርቲ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጹ።

በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ስልፍ ተካሂዷል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ የብልፅግና ፓርቲ አካታች የፖለቲካ ምህዳር መፈጠሩ በመድረኩ የገለጹት። ፓርቲ ለዓመታት በልማት ተዘንግተውና ወደኋላ ቀርተው የኖሩ አካባቢዎችን ታሪክ በመቀየር የልማት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።…

Read More

ትብብርን በማጠናከር የሚገኙ እድሎችን ወደ ሀብትነት በመቀየር የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

በዲጂታል ዘርፉ ትብብርን በማጠናከር የሚገኙ እድሎችን ወደ ሀገር ሀብትነት በመቀየር የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ሚኒስቴሩ ከህንድ ኤስ ኤ ኤ አር ሲ ማስትስ ቴክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በደመና ማስላት አገልግሎቶች፣ በሶፍትዌር ቴክኖሎጂና በፈጠራ ውስጥ የልህቀት ኢንተርፕራይዞች ግንባታ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን…

Read More