የሥራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ የሚከናወኑ ሥራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል – የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር::
በክልሎችና በከተሞች የሥራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ የሚከናወኑ ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ የሚደረገው ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ ገለጹ። በአቶ ዳንኤል ተሬሳ የተመራ የሚኒስቴሩ የባለሙያዎች ቡድን በምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኙ ክልሎች በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ የተሰሩ ሥራዎችን ተዘዋውሮ እየተመለከተ ይገኛል። ቡድኑ በዛሬው ዕለት ከድሬዳዋ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊና አመራሮች ጋር…
