Trendings

ክልላዊ የበጀት ድልድሉ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በሚያስችል መልኩ ተግባራዊ መደረግ አለበት። ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት ክልላዊ የበጀት ድልድልና የገቢ እቅድ ላይ የባለድርሻ አካላት ምክክር በቦንጋ ከተማ እየካሄደ ይገኛል። በምክክር መድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ ከዚህ ቀደም ሲተገበር የነበረው ክልላዊ የበጀት ቀመርና ድልድል ለክልል ማዕከል የካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ አነስተኛ ሚና የነበረው በመሆኑ በቀጣይ ይህንን አሰራር በማሻሻል የ2018 በጀት…

Read More

ምክር ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት 28.6 ቢሊዮን ብር ሆኖ የቀረበውን ረቂቅ የበጀት አዋጅ አጸደቀ

ረቂቅ የበጀት አዋጁን የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ የኋላሸት በላይነህ ለምክርቤቱ አቅርበዋል። የቀረበው በጀት ከክልል ገቢ የሚሰበሰብ፣ከፌዴራል መንግስት ድጎማና ከሌሎች የገቢ ምንጮች የሚገኝ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አብራርተዋል ። በዚህም መሠረት ለክልል ማዕከል መ/ቤቶች መደበኛና የካፒታል ወጪ 2.2 ቢሊዮን ፣ ለዞኖች ጥቅል በጀት 23.5 ቢሊዮን ፣ ለክልላዊ ፕሮግራሞች 2.2 ቢሊዮን ፣ ለዘላቂ…

Read More

በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፡-

በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር በሚፈጽሙ ኃይሎች ላይ የመንግሥትን ኃይል በብቸኝነት የመጠቀም ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነት ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢሰጥ፣ ሉዓላዊነትን ለመዳፈር የሚደረገውን የሻዕቢያ እንቅስቃሴ ለመግታት እየተሰራ ያሉ ስራዎችና አሁናዊ የትግራይ ክልል የሰላም፣ ጸጥታና ፖለቲካ ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ማብራሪያ ቢሰጥ፣ አካታች ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ከማን…

Read More

“ባለፉት ሶስት ወራት ከ20 የማያንሱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች በኢትዮጵያ ተካሂደዋል”

ባለፉት ሶስት ወራት ከ20 የማያንሱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ተካሂደዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስተርር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ባለፈው ዓመት ዓመቱን ሙሉ 20 ዓለም አቀፍ ኮንፈረሶችን አላካሄድንም፤ ዘንድሮ በሶስት ወር ብቻ 20 የሚደርሱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን አካሂደናል ብለዋል፡፡ በቀጣይም በርካታ ዓለም ዓቀፍ ኮንፈረንሶች በኢትዮጵያ ይካሔዳሉ ሲሉ አመላክተዋል፡፡ የኮሪደር ልማት እና በኢትዮጵያ የተፈጠረው አውድ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን ኮንፈረንሶችን…

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡-

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡- ሰላምን ማጽናት የጸጥታ ተቋማት ዋነኛ ተልዕኳቸው ነው የኢፌዴሪ የጸጥታ ተቋማት ዋነኛው ተልዕኮ ሰላምን በመላ ሀገሪቱ ማጽናት ነው፡፡ ይሄን በተመለከተ ከጸጥታ ተቋማት አመራሮች ጋር ሲደረግ የነበረው ውይይት ዛሬ ተጠቃልሏል፡፡ የኢትዮጵያ ብልጽግና እንዲሳካ ሰላምና ጸጥታ አስቻይ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ዋነኛው ግብዐትም ነው፡፡ ይሄን ለማስከበር ሕዝባችን በባህሉና በዕሴቱ ላይ ተመሥርቶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት…

Read More

ከማዕድን ሀብት የሚገኘውን ገቢ ወደ ሌሎች ልማቶች በማሸጋገር ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት ይገባል፦አቶ ፍቅሬ አማን

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ቤሮ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል። በመርሐግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ፍቅሬ፥ የክልሉ መንግሥት በአርብቶአደሩ ቀጠና ዘላቂ ሠላም በማስፈን ልማት ለማምጣት በልዩ ትኩረት እየሰራ መኾኑን ተናግረዋል። የብልፅግና ፓርቲ ለማዕድን ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት፣ የፖሊሲ ማሻሻያ እና ዕሳቤ…

Read More

የክልሉን ምርትና ማርታማነት ለማሳደግ የምርጥ ዘር አቅርቦት ላይ መጠነ ሰፊ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አቶ ማስረሻ በላቸዉ ገለጹ

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ እንዳስታወቁት፤የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል የግብርና ፓኬጆችን በተገቢዉ ሁኔታ ተግበራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምርጥ ዘርን መጠቀም ከፍተኛ ዉጤትን የሚያስገኝ በመሆኑ የምርጥ ዘር አቅርቦትን ለማሳደግ እንዲቻል የምርጥ ዘር ድርጅትን በማቋቋምና በርካታ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ዉጤታማ ተግባራትን እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚህን በፊት ምንም ዓይነት ምርጥ ዘር…

Read More

በአንድ ጀምበር ሚሊዮኖችን በመትከል የማንሰራራት ታሪካዊ ጉዞ አካል እንሁን፦ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያን ወደ ነበራት ጥንታዊ የደን ሽፋን በመመለስ አረንጓዴ ካባ ለማልበስ የጀመርነው ጥረት 7ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል፤ 7ኛ ዓመት የጥረታችንን ጅማሮ የምንዘክረዉ ደግሞ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ነው፡፡ ባለፉት 6 ዓመታት የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዟችን ኢትዮጵያውያን ከሁሉም አቅጣጫ፣ ከደጋ እስከ ቆላ በጋራ ባደረግነዉ ጥረት 40 ቢሊዮን ችግኞች በላይ ተክለናል፤ የኢትዮጵያን የደን ሽፋንም እስከ ባለፈዉ ዓመት…

Read More

ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፡- •እያንዳንዱ ችግር ብለን የምናነሳው ሀሳብ አሁን የተፈጠረ ብቻ ሳይሆን ተሳስሮ የመጣ ስለሆነ እነዚህን ጉዳዮች ከስር መሰረቱ መገንዘብና ማየት ካልቻልን መፍትሔ ለማምጣት እንቸገራለን፡፡ •ልንግባባበት የሚገባው ዋና ጉዳይ ችግሮቻችን በጋራና እኩል የምንገነዘባቸውና የምንረዳቸው ከሆኑ ጉዟችን ወደ መፍትሔ ሊሆን ይችላል፡፡…

Read More

ኡሲቃ የተፈጥሮ ፍል ውሃ

ኡሱቃ የተፈጥሮ ፍል ውሃ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን በሸኮ ወረዳ ሺሚ ቀበሌ ኡሱቃ መንደር ይገኛል። ፍል ውሃው በአረንጓዴና ውብ በሆነው ደን የተከበበ ሲሆን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በመምጣት በርካታ ሰዎች እንደሚጎበኙም ተጠቁሟል። የተፈጥሮ ፍል ውሃው በቁጥር 44 ምንጭ ያለውና ለተለያዩ በሽታዎች እንደ ፈውስ ያገለግላል። በየዓመቱ ከተለያዩ አከባቢዎች የሚመጡ ሰዎች ከማስጎብኘት ባለፈ የተፈጥሮ…

Read More