አሁናዊ ያልተገባ የኑሮ ውድነትን በመቀነስ ማህበረሰብን በተመጣጣኝ ዋጋ፤በዓይነት ፣ በመጠን እና በጥራት የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ
በቦንጋ ከተማ ሁለተኛ ሳምንት የእሁድ ገበያ (Sunday market) መጠኑንና ዓይነቱን ጨምሮ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በባለፈው ሳምንት የዞን እና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር መከናወኑን ያስታወሱት የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ንግድ እና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወዳጆ ደሳለኝ ሁለተኛ ሳምንት የእሁድ ገበያ (Sunday market) መጠኑና ዓይነቱን ጨምሮ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። አሁናዊ ያልተገባ የኑሮ ውድነትን በማስተካከል…
