የክልሉ ትምህርት ቢሮ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ፖርታል በይፋ አስጀመረ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ ከኢፌዴሪ ትምህርት ምኒስቴር ጋር በመተባበር የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ፖርታል በይፋ አስጀመሯል። በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር ታርጫ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሄደው ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሃግብር የተገኙ የክልሉ ትምህርት ቢሮ የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ባህሩ አለሙ ፕሮጀክቱ የተማሪዎችን የእንግሊዝኛ ክህሎት ከማሻሻልም ባሻገር በውጤት መሻሻል ላይ ያለው…
መፅሐፍ ቋሚ እውቀትን ለመፍጠርና ከትውልድ ወደትውልድ ለማስተላለፍ አጋዥ መሆኑ ተገለፀ።
የኢትዮጵያ ቤተመጻሕፍት እና ቤተመዛግብት የተለያዩ መጽሐፍት ለምዕራብ ኦሞ ዞን አስረክቧል። በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተመጽሐፍት አገልግሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አባተ ካሳው እንደተናገሩት፤ አገልግሎቱ እውቀትን በማከማቸትና ለሚቀጥለው ትውልድ በማስተላለፍ ለ80 ዓመታት መስራቱን ተናግረዋል። ማንበብ እየፈለጉ መፅሐፍት የማያገኙ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን አንስተው፤ አገልግሎቱ በትምህርት፣ በማረሚያ ቤቶችና በህዝብ ቤተመጻሕፍቶች የንባብ ባህልን ለማዳበር እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ዛሬ ላይ የተደረገው…
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ31 ወርቅ አምራችና 1 ወርቅ አቅራቢ ማህበር ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ31 ወርቅ አምራችና 1 ወርቅ አቅራቢ ማህበር ላይ እርምጃ መወሰዱ የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ገልጿል፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገ/ማሪያም ሰጠኝ ዕርምጃ የተወሰደባቸዉ ከባለፈው 2016 በጀት ዓመት ጀምሮ ምንም አይነት ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ያላስገቡና የዕቅዳቸውን ከ10% በታች አፈፃፀም ያሳዩ ማህበራት እና ወርቅ አቅራቢያ መሆናቸዉን ነው አቶ ገ/ማሪያም የጠቆሙት፡፡ እነዚህ…
የዘመኑ አርበኝነት በራስ ክህሎት ኢትዮጵያን ማነጽ ነው- ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል
በዘመኑ አርበኝነት በራሳችን ክህሎት የበለጸገች ኢትዮጵያን ማነጽ እንደሚቻል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዘጋጅነት “ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች” በሚል መሪ ሃሳብ “ክህሎት ስለ ኢትዮጵያ” ምዕራፍ ሁለት የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ለመድረኩ መነሻነት የተሰናዳውን የኢንዱስትሪ፣ የስራ ዕድል ፈጠራና የክህሎት ልማት ተግባራትን የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ መርቀው ከፍተዋል።…
ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ።
የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀምሯል። ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባኤው የምክር ቤቱን ጨምሮ የአስፈጻሚ አካላት የመጀመሪያ ግማሽ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ለምክር ቤቱ ቀርቦ ተገምግሞ ይፀድቃል ተብሏል። ጉባኤው ለ2 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ የልማት ስራዎች ጉብኝት ጨምሮ ልዩ ልዩ ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ ከወጣው…
የብልፅግና ወጣቶች ክንፍ የስያሜ ለውጡን ይፋ አደረገ
የብልፅግና ወጣቶች ክንፍ ባለፈው ወር በፓርቲው 2ተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በተቀመጡ አቅጣጫዎች ዙሪያ እየመከረ ይገኛል። በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የብልፅግና ወጣቶች ክንፍ ምክር ቤት በፓርቲው ጉባኤ በተወሰነው መሰረት የአደረጃጀቱ መጠሪያ የወጣቶች ሊግ ከነበረበት የወጣቶች ክንፍ ተብሎ ጥቅም ላይ እንዲውል አቅጣጫ ሰጥቷል። ምክር ቤቱ ሶስት አጀንዳዎችን ማለትም ፦ የ6ወራት አፈፃፀም ግምገማ፣ በመላው ሀገሪቱ የወጣቱን ተጠቃሚነት…
በበጀት ዓመቱ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች 30 ሚሊዮን ዜጎችን ለማመካከር እቅድ ይዞ እየሠራ እንደሚገኝ የሠላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በሚዛን አማን ከተማ በማህበረሰብ ተኮር ምክክር ዉጤታማነት ዙሪያ በሠላም ሚኒስቴር አማካይነት ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየዉ የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል። በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከ6ቱም ዞኖች ለተወጣጡ የሠላምና ጸጥታ ተቋም ባለሙያዎችና የማህበረሰብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሙያተኞች የአመቻችነት ሥልጠና እንዲወስዱ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ተግባራት ውጤታማነት ዙሪያም አቅጣጫ ተቀምጧል። የሥልጠናው ተሳትፊዎች በቆይታቸው በቂ…
በጥምር ግብርና አትክልትና ፍራፍሬ በማልማት ውጤታማ መሆናቸውን በዘርፉ የተሠማሩ አርሶአደሮች ተናገሩ።
በዳውሮ ዞን ቶጫ ወረዳ በኦክሊ-ዳልባ ቀበሌ በጥምር ግብርና አትክልትና ፍራፍሬ በማልማት የተሠማሩ አርሶ አደሮች መካከል ሞዴል አርሶአደር አቶ አለማየሁ ድልቦ እና ተይበላ ዶራሞ እንደተናገሩት፤ በበጋ መስኖ አትክልትና ፍራፍሬ ማልማት አይቻልም የሚለው አመለካከት ተቀይሮ በአንድ ማሳ ጥምዝ፣ ኮረሩማ፣ ድንች፣ ቲማቲም እና በቆሎ በማምረት ላይ መሰማራታቸውን አንስተዋል። አርሶ አደሮቹ በሌላ በኩል አቦካዶ፣ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ ቡርቱካን፣ ሎሚ እና…
በአዳማ የተጀመረዉ የስማርት ሲቲ ግንባታ ቀልጣፋ መንግሥታዊ አገልግሎት መስጠት ማስቻሉ ተገለጸ
“ዓላማ ተኮር፣ የተናበበ እና የተቀናጀ የተግባቦት ሥርዓት ለእመርታዊ ዕድገት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ያለዉ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የጋራ ጉባኤ ተሳታፊዎች የአዳማ ከተማን “ስማርት አዳማ ፕሮጀክትን” ጎብኝተዋል፡፡ የከተማዋ የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ የመንግሥትን አሠራር ሥርዓት ከማዘመኑም በላይ ለማኅበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ያስቻለ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር ) ገልጸዋል፡፡ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሠሩ ያሉ…
