Trendings

Getenesh Gebeyehu

ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሹዌ ቢንግ ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት በሁኔታዎች የማይቀያየር ስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ ላይ መድረሱን በመግለጽ፤ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ለምታደርገው ጥረት የቻይናን ድጋፍ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም (FOCAC) የተቀመጡ ግቦችን ከአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ…

Read More

የትምህርት ሴክተር ማነቆዎችን ለመፍታት እየተተገበረ ያለው ማሻሻያ አውንታዊ ለውጥ እያሳየ ይገኛል፦ ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

መንግሥት የትምህርት ሴክተር ማነቆዎችን ለመፍታት እየተገበረ ያለው ማሻሻያ አውንታዊ ለውጥ እያሳየ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ”የትምህርት ጥራት እምርታ ለሁለንተናዊ ብልጽግና!” በሚል መርህ ቃል በተዘጋጀው የትምህርት ሴክተር ጉባኤ ላይ ነው። ትምህርት የሀገር ተረካቢ የሆኑ ዜጎች በእውቀት፣በክህሎት እና በስነ-ምግባር ታንጸው የሚወጡበት…

Read More

የክልሉ ትምህርት ቢሮ 1ኛ ዙር የትምህርት ሴክተር ጉባኤ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል

”የትምህርት ጥራት እምርታ ለሁለንተናዊ ብልጽግና!” በሚል መር ቃል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጰያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀው 1ኛ ዙር የትምህርት ሴክተር ጉባኤ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ የ1ኛ ዙር የትምህርት ሴክተር ጉባኤ ክልላዊ የትምህርት ልማት ሥራዎች፣ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድም ተገልጿል። በጉባኤው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር…

Read More

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ወደ ሰላማዊ መድረክ እንዲመጡ ጥሪ አቀረቡ

ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ፅንፈኝነት እና ግጭት ማንንም እንደማይጠቅም በመገንዘብ ወደሰላማዊ መድረክ እንዲመጡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ መንግሥት ሁልጊዜም ቢሆን ለሰላም በሩ ክፍት በመሆኑን አረጋግጠዋል። ዛሬ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች፣ የገጠር ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ህዝቡ ”ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ በነቂስ ወጥቶ ላሳየው…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ ከፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለዳዉሮና ኮንታ ገቢዎች መምሪያ ለሚገኙ ባለሙያዎች ሥልጠና እየሰጠ ነዉ

በሥልጠናው የተገኙ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የደንበኛ አገልግሎት የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንዱ ታደሰ እንደተናገሩት ከየካቲት 1 ጀምሮ በክልሉ ሁሉም የገቢ ሰብሳቢ ተቋማት በአንድ የአሠራር ሥርዓት በመታገዝ ወጥ አካሄድ እንዲኖር ይሠራል ብለዋል። በቀጣይም በQR CODE የተመዘገበና የተረጋገጠ የማኑዋል ደረሰኝ በኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ የሚተካ ይሆናልም ስሉ ገልጸዋል። ከታህሣሥ 30 ጀምሮ የታክስ ሪፖርት ከየተቋማቱ በማኑዋል…

Read More

ዞናዊ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመፈፀምና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ዞናዊ የንቅናቄ መድረክ በሚዛን አማን ተካሄደ።

በቀጣይም 8700 ኩንታል ለስትራቴጂክ የምግብ ሰብል መጠባበቂያ ክምችት ከ240 ሄክታር በላይ መሬት ላይ እንደሚመረትም በንቅናቄ መድረኩ ተገልጿል። የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደግፌ ኩድን መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት እንደ ሀገር ተረጂነትን ማስቀረት የሀገር ሉአላዊነትና ክብርን ማስጠበቅ ነው ብለዋል። መንግስትም ተረጂነትና ልመናን የሚፈፀየፍ ትውልድና ሀገር ለመፍጠር በገጠርና በከተማ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ…

Read More

ዶክተር ለገሰ ቱሉ ሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ገብተዋል

የኢፌዲሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ገብተው የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ። በወረዳዉ ዮኪጭጭ ቀበሌ በሴቶች አደረጃጀት እየተከናወኑ የሚገኙ የማር መንደርን ጎብኝተዋል። ማህበሩ 78 ዘመናዊ የንብ ቀፎ ያሉት ሲሆን በዓመት 500 ኪ.ግ ማር እንደሚያገኙ፣ማርን ከማምረት ባለፈ በግ፣ፍየል፣በሬ እንደሚያደልቡ፣የበጋ መስኖ ስንዴን በማምረት ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል። በ2016…

Read More

የብሔራዊ ባንክ አዋጅ ፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዋጅን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምቤት በዛሬው እለት ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ነው የብሔራዊ ባንክ አዋጅን ያፀደቀው፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ የምክር ቤት አባላት ላነሱት ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ÷ አዋጁ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተረጋጋ ሆኖና ጥራቱን ጠብቆ እንዲሄድ ያስችላል ብለዋል፡፡ አዋጁ የባንኩን ዓላማ በግልጽ እንዳስቀመጠ ገልጸው÷ የባንኩ…

Read More

ቆይታ ከእኛ ጋር!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተፈጥሮ ጸጋዎች የበለጸገ፤ የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውሀ ባለቤት፤ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ እጅግ ጥቅጠቅ ያሉ የተፈጥሮ ደኖች ያሉበት፤ ወንዞች፣ ፏፏቴዎች፣ ሐይቆች፣ ብርቅዬ እንስሳትና አዕዋፋት እንዲሁም በርካታ የተፈጥሮ ስጦታዎች ያሉበት ክልል ነው፡፡ ክልሉ ከሚታወቅባቸው የከርሰ ምድር ጸጋዎች መካከል የድንጋይ ከሰል፣ የወርቅ ማዕድን፣የኮንስትራክሽን ማዕድናት፣ የብረት ማዕድናትና ሌሎች ጸጋዎች በስፋት የሚገኙበት ድንቅ ምድር…

Read More

የኢፌዲሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በሸካ ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ

በጉብኝታቸውም በሸካ ዞን የኪ ወረዳ በጪ ቀበሌ በአርሶ አደሮች በክላስተር የለማ የሩዝ ምርት አሰባሰብ ሂዴትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በተደራጁ ወጣቶች በፊደና አዲስ ብርሃን ቀበሌ እየለማ የሚገኙ የቅመማ ቅመም ( ቁንዶ በርበሬ፣እርድ) ማሳም የጉብኝቱ አካል ነበሩ። ጥምር እርሻ(ሙዝ ፣ፓፓያ፣አናናስና ቡና)፣የማር መንደርን የጎበኙ ሲሆን በኩብጦ ቀበሌ የአቶ ደረጀ ዳልቶ የቡና እንዱስትሪ የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል። ዶክተር ለገሰ ቱሉ በጉብኝቱ…

Read More