የዩኒቨርሲቲዎች በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ የሚመደብ ይሆናል -ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለፁ። በትምህርት ዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በተቀናጀ መልኩ ማሻሻል የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል። ስምምነቱን ትምህርት ሚኒስቴርና 47 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የቦርድ ሰብሳቢዎችና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ፈርመውታል። የትምህርት ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት፥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በመሰረታዊነት ለመቀየር የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ወሳኝ ነው ብለዋል። በተለይም ብቃት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራትና…
