የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በአውሮፓውያኑ የ2025 አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ወራቶች በኢትዮጵያን እና ሶማሊያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ማቀዳቸው ተገልጿል፡፡ ጉብኝቱ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አደራዳሪነት ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ የታቀደ ነው ተብሏል፡፡ ባሳለፍነው ቅዳሜ ከቱርክ ወጣቶች ጋር ቆይታ የነበራቸው ፕሬዝዳንቱ፤ የአንካራው ስምምነት 7 ሰዓታትን የፈጀ እንደነበር በመግለፅ በሁለቱ ሀገራት ትብብር ከስምምነት መደረሱን ጠቁመዋል፡፡…
