የዩናይትድ ኪንግደም የግብርና ንግድ ልዑክ በኢትዮጵያ በግብርና ኢንቨስትመንት መስኮች መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ
የዩናይትድ ኪንግደም የግብርና ንግድ ልዑክ (UK Agribusiness Trade Mission) በኢትዮጵያ በግብርና የኢንቨስትመንት መስኮች የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ። የግብርና ሚኒስትር ከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪ ጫላ ሆርዶፋ(ዶ/ር) ከልዑኩ ጋር በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል። በመድረኩ በወተት ሀብት፣ በዶሮ፣ በማር፣ በእንስሳት ጤና፣ በዘርና በእንስሳት መኖ ልማት የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ምክክር ተደርጓል። ለልዑክ ቡድኑ በኢትዮጵያ ስላሉ የግብርናው የኢንቨስትመንት እድሎች…
