በአቪዬሽን አሰራር ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ “ዳዊት ድሪባ በዳኔ” በሚል ስም የ3 ጊዜ የሞት ፍርደኛ እንደነበር ፖሊስ አስታወቀ
ሰሞኑን በአቪዬሽን አሰራር ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ፣ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ “ዳዊት ድሪባ በዳኔ” በሚል ስም 3 ጊዜ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት እንደነበር ፖሊስ ገልጿል፡፡ ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ እንደተቻለው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ታሕሳስ 25 ቀን 1999…
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የኢትዮጵያን ምርት የመግዛት ባህል ማዳበር ያሰፈልጋል፦ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የኢትዮጵያን ምርት የመግዛት ባህል ማዳበር ይገባል ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር “የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ሀሳብ ካዘጋጀው የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽን ጎን ለጎን ትኩረቱን የጥራት መሰረተ ልማት ላይ ያደረገ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት፤ ጥራት ለምርቶች…
ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እና ከጋምቤላ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ለተውጣጡ ዲኖች ፣ አሰልጣኞችና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።
የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ዞኑ በተፈጥሮ ሀብቱ የበለፀገ በተለይም በተፈጥሮ ደን፣ በቱሪስት መስህቦች፣ ቡናና ቅመማ ቅመም፣ በማርና በሻይ ምርት የሚታወቅና ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ብሎም ኤክስፖርት በማድረግ ከአካባቢው አልፎ ለሀገር አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል። አክለውም ዞኑ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች…
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ልማት የግሉን ዘርፍ በስፋት እንዲሳተፍ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አገር አቀፍ የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽንን ምክንያት በማድረግ “አረንጓዴ ኢኮኖሚን እውን በማደረግ ሂደት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሚና “በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት አካሂዷል። ከውይይቱ ጎን ለጎንም በኃይል ቁጠባ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡና፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሽያጭ የፈጸሙ ኩባንያዎችና ድርጅቶች እውቅና ተሰጥቷል። በሥነ-ስርዓቱ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶክተር)፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሰሃረላ…
ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለመገንባት የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራን አቅም መገንባት ላይ ትኩረት ተደርጓል
ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለመገንባት የቴክኒክና ሙያ የአሰልጣኝ መምህራን አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት መደረጉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። ሚኒስቴሩ ከነገ ጀምሮ “ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ኃሳብ ለ12 ቀናት የሚቆይ ሥልጠና እንደሚያስጀምር አስታውቋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ ሥልጠናው አዲስ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ ወደ ሥራ መግባቱን መሠረት ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን…
በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች እየተከናወነ ያለው የበጎ ተግባራት ዜጎችን በተጨባጭ ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል:-ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሁሉም አከባቢዎች እየተከናወነ ያለው የበጎ ተግባራት ዜጎችን በተጨባጭ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገልጸዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተደድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እና የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በክልሉ በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ አስጀምረዋል።…
fvfdvg
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ እና የኢፌዲሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አቅሜ ደካሞች የቤት ግንባታዉን ዛሬ በይፋ በዳዉሮ ዞን በታርጫ ከተማ አስጀምረዋል። የኢፌዲሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከGGGI ከተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያስገነባው አምስት ደረጃቸውን የጠበቁ የመኖሪያ ቤቶች ሲጠናቀቁ በውስጣቸው ሙሉ የቤት ውስጥ…
በዶክተር መቅደስ ዳባ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በ74ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ እየተሳተፈ ነው
በኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በ74ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ እየተሳተፈ ነው። የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ዛሬ ኮንጎ ሪፐብሊክ በብራዛቪል መካሄድ ጀምሯል። እስከ ነሀሴ 25/2016 ዓ.ም በሚቆየው መድረክ በጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የተመራዉ የኢትዮጵያ ልዑክም በመድረኩ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ዛሬ በብራዛቪል ከተማ በይፋ በተጀመረው 74ኛው…
የንግድ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ ነው – ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)
የንግድ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የተደገፈና የተደራጀ የማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ። ዛሬ የአገር ውስጥ ንግድን የተመለከተ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው። በውይይቱ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)፣ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት፣ ምሁራን፣ የሸማች ማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል። የንግድ ስርዓቱ ከብልሹ አሰራሮች የፀዳና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ሚኒስትሩ…
