ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረች
በኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል አለ የጤና ሚኒስቴር፡፡ የኢትዮጵያ ድንገተኛ የማሕበረሰብ ጤና አደጋ ፈጣን ምላሽና አመራር ስኬቶች እንዲሁም የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ቁጥጥር ማብሰሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡ በመርሐ ግብሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ አጋር አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡…
