በበጀት ዓመቱ 470 ቶን ቡና ወደ ማዕከላዊው ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
በወረዳው ከቅርብ ዓመታት በፊት የቡና ልማት ብዙም ያልተለመደና ከ600 ሄክታር ያልበለጠ የጫካ ቡና መኖሩን በማስታወስ አሁን በተሰጠው ትኩረት ከ10,400 ሄክታር በላይ ማሳ በቡና መሸፈኑን የጣሎ ወረዳ ግብርና ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ጽህፈት ኃላፊ አቶ አፋወርቅ አደመ ገልጸዋል። በወረዳው አሁን በሁሉም ቀበሌዎች ማልማት የተጀመረ መሆኑን በመጥቀስ ከዚህ ውስጥ አራቱ ቡናን ስፔሻላይዝ በማድረግ የሚያመርቱ መሆናቸውን ተናግረዋል…
