የባሕር በር ጥያቄ የውስጥ ልዩነቶችን የሚሻገር የትውልድ ጥያቄ ነው
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የውስጥ ልዩነቶችን የሚሻገር የትውልድ ጥያቄ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ፣ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። ከምክር ቤት አባላቱ ለሚኒስትሩ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል፤ ኢትዮጵያ በታሪካዊ ስህተትና ግፍ…
